25 ጥቅምት 2014

RSS Facebook Twitter Linkedin Digg Yahoo Delicious

ሐሙስ, 26 ታህሳስ 2013 14:43

ሂፐታይተስ ሲ የተባለውን የጉበት በሽታ ለመከላከል የሚያስችል አዲስ መድሃኒት ይፋ ተደረገ

ይህን ዜና ይመዝኑት
(0 ምርጫዎች)

አዲስ አበባ ታህሳስ 17/2006 ሂፐታይተስ ሲ የተባለውን የጉበት በሽታ ለመከላከል የሚያስችል አዲስ መድሃኒት በአሜሪካና አውሮፓ ይፋ ተደረገ፡፡

ከፍተኛ ዋጋ የሚጠይቀውን ይህንን መደሀኒት በሽታው በፍጥነት ጉዳት እያደረሰ ባለበት በማደግ ላይ ባሉ አገሮችም እንዲሰራጭ ጉዳዩ ባሳሰባቸው አካላት ጥሪ ቀርቧል፡፡

እንደ አለም ጤና ድርጅት ሪፖርት 185 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች በሄፐታየተስ ሲ በተባለ የጉበት በሽታ ይሰቃያሉ፡፡

በሽታው በባህሪው ለረዥም ጊዜ ሳይታወቅና ምልክት ሳያሳይ  በሰውነት ውስጥ የመቆየት አቅም ያለውና ድንገት በሚሰማ ከፍተኛ ህመም የሚገለጸ መሆኑንም ባለሞያዎቹ ይናገራሉ፡፡

በዚህ ምክንያት በየአመቱ በበሽታው ምክንያት 350 ሺህ ሰዎች ለህልፈተ ህይወት እንደሚዳርግና ከሶስት እስከ አራት ሚሊዮን የሚሆኑ አዲስ ሰዎችም በዚሁ እንደሚያዙ ሪፖርቱ ያመለክታል፡፡

አሁን ገበያ ላይ ያለው መደሃኒትም በመጠኑም ቢሆን መፍትሄ የሚሰጥ ቢሆንም ከመድሃኒቱ ጋር ተያይዘው የሚመጡ የጎንዮሽ በሸታዎች ግን ከህመሙ የመዳን ተስፋን አሳጥቶታል፡፡

ጊኒት ጊሊድ በተባለ የመድሃኒት ፋብሪካ አማካኝነት ምርቱ እየቀረበ ያለው ሶፎ ቦቨር የተባለው ይህው አዲስ መድሃኒት የጎንዮሽ ተጽኖው አነስተኛና ለበሸታው ሙሉ ለሙሉ መፍትሄ የሚሰጥ ተብሎለታል፡፡

ሆኖም መድሃኒቶ ዋጋ በጣም ከፍተኛ የሚባልና ለአንድ ጊዜ ህክምና 80 ሺህ ዶላር የሚያወጣ እንደሆነም ታውቋል፡፡ ከበሽታው ሙሉ ለሙሉ ለመድሃንም ከአራት ጊዜ በላይ መድሃኒቱን መውሰድ ያስፈልጋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ከኤችአይቪ/ኤድስ በላይ ህብረተሰቡን እየጎዳ ያለውን ሂፐታይተስ ሲ የጉበት በሽታም ለመከላከል የሚመለከታቸው ተቋማትና መንግስታት ትኩረት ሰጥተው መድሃኒቱን ተመጣጣኝና አነስተኛ በሆነ ዋጋ ለሁሉም አለም እንዲዳረስ መስራት እንደሚያስፈልግ ኦል አፍሪካ ዶት ኮምን ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የተነበበው 528 ጊዜ ለመጨረሻ ጊዜ የተሻሻለው ሐሙስ, 26 ታህሳስ 2013 16:36

አስተያየቶን ይላኩ

የኮከብ ምልክት(*)ያለበት ቦታ ሳይሞላ መታለፍ የለበትም። በተጨማሪም HTML ኮድ ማስገባት የተከለከለ ነው።