አርዕስተ ዜና

በጥር ወር በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ደረቅ፣ጸሀያማና ነፋሻማ የአየር ፀባይ ያመዝንባቸዋል

02 Jan 2018
825 times

አዲስ አበባ ታህሳስ 24/2010 በጥር ወር በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ደረቅ፣ጸሀያማና ነፋሻማ የአየር ፀባይ እንደሚያመዝን ብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

በጥር ወር በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ደረቃማው የአየር ሁኔታ አመዝኖ በመዋሉ ለሰብል ስብሰባና ድህረ ሰብል ስብሰባ ምቹ እንደሆነ ኤጀንሲው ለኢዜአ በላከው መግለጫ አስታውቋል።

በጥር ወር  የበጋው ደረቅ፣ጸሀያማና ነፋሻማ የአየር ጠባይ በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች አመዝኖ እንደሚውል ኤጀንሲው አመላክቷል፡፡

በአንዳንድ ደጋማ አካባቢዎች የማለዳው ቅዝቃዜ ቀጣይነት እንደሚኖረው የተገለጸ ሲሆን፤ይህም እድገታቸውን ባልጨረሱ የሰብልና የፍራፍሬ ሰብሎች ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንዳያሳድሩ አርሶ አደሮች የአካባቢያቸውን ሙቀት ለማሻሻል ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉም መክሯል፡፡

ከወሩ አጋማሽ በኋላ ከደመና ሽፋን መጨመር ጋር ተያይዞ በጥቂት የምዕራብ ኦሮሚያና የምስራቅ አማራ ክልሎች ላይ አነስተኛ መጠን ያለው ዝናብ ሊኖር እንደሚችልም ትንበያው ያስረዳል፡፡

በውሃው ዘርፍ በወሩ መጨረሻ አካባቢ የአዋሽ ስምጥ ሸለቆና ምዕራባዊ ክፍል፣ገናሌ ዳዋ እንዲሁም የላይኛው የአባይ ተፋሰሶች በከፊል መጠነኛ የእርጥበት  እንደሚኖራቸው ይጠበቃል፡፡

ይህም ለግጦሽ ሳርና ለአነስተኛ ወንዞች አዎንታዊ ጠቀሜታ እንደሚኖረውም ተገልጿል፡፡

ከበልግ ወቅት መቃረብ ጋር ተያይዞ በመደበኛ ሁኔታ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል፣ደቡብ፣ምዕራብ፣መካክለኛውና ምስራቅ ኦሮሚያ አንዳንድ ቦታዎች እንዲሁም ምስራቅ አማራ ስፍራዎች አነስተኛ ዝናብ እንደሚያገኙ መረጃው ያመለክታል፡፡

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ