አርዕስተ ዜና

ቴክኖሎጂዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለአርሶ አደሩ እያቀረብን ነው - ኅብረት ሥራ ዩኒዬኖቹ

28 Nov 2017
1150 times

አርሶ አደሩ ዘመናዊ የእርሻ ቴክኖሎጂዎችን እንዲጠቀም በማላመድና በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ረገድ የመሪነት ሚና እየተጫወቱ መሆኑን የዳሞትና የጎዛምን የህብረት ሥራ ዩኒዬኖች ገለጹ።

በምዕራብ ጎጃም ቡሬ ከተማ በ1994 ዓ.ም የተቋቋመው የዳሞት ሁለገብ የገበሬዎች ኅብረት ሥራ ዩኒየን ከ143 ሺህ በላይ አባላትን ያቀፈ ሲሆን፤ ካፒታሉም ከ108 ሚሊዮን ብር በላይ ደርሷል።

ዩኒየኑ ምርትና ምርታማነትንና ተጠቃሚነት ለማሳደግ ከተሰማራባቸው ሁለገብ ዘርፎች መካከል አንዱ የዘመናዊ እርሻ ቴክኖሎጂዎችን ማስተዋወቅ ነው።

የዩኒየኑ ስራ አስከያጅ አቶ ጌታቸው እሸቱ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ የአባላቱን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ በሜካናይዜሽን ቴክኖሎጂዎችን በማስተዋወቅና በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ረገድ በትኩረት እየሰራ ይገኛል።

ለአብነትም የስንዴ መሰብሰቢያ ኮምባይነር፣ የእርሻ ትራክተርና አነስተኛ የበቆሎ መፈልፈያ ማሽኖቸን ግዥ መፈፀሙን ተናግረዋል።

ትራክተሮቹ በቅርብ ሳምንታት ስራ እንደሚጀምሩ የጠቆሙት ስራ አስኪያጁ፤ ካሁን በፊት ሁለት አነስተኛ የበቆሎ መፈልፈያ ማሽኖች መግባታቸውንና ሌሎች 10 ማሽኖቸን ለማስገባት ትዕዛዝ መሰጠቱን ገልጸዋል።

በ1996 ዓ.ም በምሥራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ማርቆስ ከተማ የተቋቋመውና ከ125 ሺህ በላይ አባላትን ያቀፈው የጎዛምን ሁለገብ የገበሬዎች ኅብረት ሥራ ዩኒዬን ሌላው በዘመናዊ የእርሻ ቴክኖሎጂ  አቅርቦት የተሰማራ ማህበር ነው።

የዩኒዬኑ ሥራ አስኪያጅ አቶ ጌቱ ባሴ ዩኒየኑ ከዚህ በፊት በግብዓት አቅርቦት፣ በመኖ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ እንዲሁም በቀን አንድ ሺህ ሁለት መቶ ኩንታል ስንዴ የሚፈጭ የዱቄት ፋብሪካ ገንብቶ እየሰራ መሆኑን ይናገራሉ።

በዚህ ዓመት የአርሶ አደሩን ቁልፍ ፍላጎት በመለየት በእርሻ መካናይዜሽን እንዲሳተፍና "የቴክኖሎጂ ፍላጎቱን ለማርካት የምርት መሰብሰቢያና የእርሻ መሳሪያዎችን ማቅረብ ጀምሯል ነው" ያሉት።

ስራ የጀመሩት ሁለቱ ኮምባይነሮች ስምንት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ብር ወጭ እንደተደረገባቸው የገለጹት አቶ ጌቱ፤ ዩኒየኑ በቀጣይ ከራሱ ካፒታል በተጨማሪ በመንግስት ዋስትና በተፈቀደ 10 ሚሊዮን ብር አራት ኮምባይነሮች ለመግዛት ማቀዱን ተናግረዋል።

የእርሻ ትራክተሮችን ደግሞ ዩኒዬኑ ባቀፋቸው ሰባት ወረዳዎች ለማዳረስ መዘጋጀቱን አብራርተዋል።

ያም ሆኖ የኅብረት ሥራ ዩኒዬኖች አሁን ባላቸው የቴክኖሎጂ አቅርቦት የአርሶ አደሩን ፍላጎት ማሟላት እንዳልተቻለ ይናገራሉ።

የፋይናንስ፣ የመሳሪያዎች ጥገና ባለሙያ፣ በአርሶ አደሩ ማሳ አካባቢ የመሰረተ ልማት አለመሟላት በስራቸው ላይ ተጽዕኖ እንዳሳደሩ ይናገራሉ።

የዳሞት ዩኒየን ሥራ እስኪያጅ አቶ ጌታቸው እሸቱ በቴክኖሎጂ አቅርቦት ረገድ ያለው የአርሶ አደሩ ፍላጎት ከፍተኛ በመሆኑ የግል ባለሀብቱም መግባት እንዳለበት ይናገራሉ።

የጎዛምን ዩኒዬን ስራስኪያጅ አቶ ጌቱ ባሴ በበኩላቸው የአርሶ አደሩ ፍላጎት ከፍተኛ በመሆኑ ፍላጎቱን ለማሟላት የካፒታል፤ የስልጠና እንዲሁም የመሰረተ ልማት ችግር እንቅፋቶች መሆናቸውን ጠቁመዋል።

በወቅቱ የስንዴ መሰብሰቢያ ዋጋ በኩንታል 70 ብር ቢሆንም፤ ኅብረት ሥራ ዩኒየኖቹ ባስገቧቸው የስንዴ ሰብል መሰብሰቢያ ኮምባይነሮች በኩንታል 70 ብር ተመጣጣኝ ዋጋ አገልግሎት ይሰጣሉ።

 

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ