አርዕስተ ዜና

የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ ምክር ቤት የ546 ምርት ደረጃዎችን አፀደቀ

አዲስ አበባ መጋቢት 25/2010  የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ ምክር ቤት በሰባት የምርት ስራ ዘርፎች ስር የሚገኙ 546 ማፅደቁን አስታወቀ።

ሸማቹ ህብረተሰብ ለምግብነት የሚውሉ እቃዎችን ሲገዛ የደረጃዎች ኤጀንሲ ምልክት መኖሩን አይቶ እንዲገዛ ኤጀነሲው ጥሪ አቅርቧል።

የኤጀንሲው የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ይስማ ጅሩ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳሉት በተለይም ሸማቹ ህብረተሰብ ለምግብነት የሚውሉ እቃዎችን ሲገዛ የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ ምልክት መኖሩን አይቶ እና አረጋግጦ እንዲገዛ መልዕክት አስተላልፏል።

ኤጀንሲው ካጸደቃቸው ደረጃዎች ውስጥ 267 አዲስ፣ 76 የተከለሱ፣ 203 በነበሩበት የሚቀጥሉ እና 41 አስገዳጅ ደረጃዎች ናቸው።

አስገዳጅ ደረጃዎች የፀደቁት ከሰው ህይወትና አካባቢ ጋር በቀጥታ ግንኙነት ባላቸው ምርቶች ላይ ሲሆን የለስላሳ መጠጦች፣ ጭማቂዎችና የህፃናት ምግቦችን ያካተቱ ናቸው።

ኤጀንሲው ያፀደቃቸው ደረጃዎች በኮንስትራክሽንና ሲቪል ኢንጂነሪንግ ዘርፍ፣ በአካባቢና ጤና ደህንነት ዘርፍ፣ በኤሌክትሮ ሜካኒካል የደረጃ ዝግጅት ዘርፍ፣ በመሰረታዊና አጠቃላይ የደረጃ ዝግጅት ዘርፍ እንዲሁም በግብርና እና ምግብ ዘርፍ ናቸው።

ከዚህ በተጨማሪም በኬሚካልና ኬሚካል ውጤቶች እንዲሁም በጨርቃ ጨርቅና ቆዳ ውጤቶች ዘርፎችን የሚጨምር ሲሆን የደረጃዎቹ መውጣት በገቢና በወጪ ምርቶች ላይ ደረጃውን የጠበቀ ምርት እንዲኖርና ጤናማ የንግድ ውድድር እንዲኖር ትልቅ ሚና አላቸው ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪም የህብረተሰቡን ጤናና ደህንነት፣ አካባቢ ጥበቃና የሸማቾችን ጥቅም ከማስጠበቅ ረገድም ትልቅ ጥቅም ይኖራቸዋል ተብሏል።

 

 

Last modified on Tuesday, 03 April 2018 19:11
Rate this item
(1 Vote)

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን