አርዕስተ ዜና
×

Warning

JUser: :_load: Unable to load user with ID: 452

ማዕከሉ የጉምዝ በግ ዝርያን ጠብቆ የስጋ ምርታማነቱን የሚያሻሽል ጥናት እያካሄደ ነው

07 Oct 2017
2227 times

ጎንደር መስከረም 27/2010 የጎንደር ግብርና ምርምር ማዕከል የጉምዝ በግ ዝርያን በመጠበቅ የስጋ ምርታማነቱን ለማሻሻል የሚያስችል ጥናት እያካሄደ መሆኑን አስታወቀ፡፡

በማዕከሉ የእንስሳት ዝርያ ማሻሻል ተመራማሪ አቶ አላዩ ኪዳኔ እንደተናገሩት በቆላማ የአየር ንብረት ክልል መኖር የሚችለው የጉምዝ በግ ዝርያ በስጋ ምርታማነቱ ከደጋ በጎች የተሻለ ነው፡፡

በስጋ ምርታማነቱ የሚታወቀውን የበግ ዝርያ በመጠበቅና የስጋ ምርታማነቱን ማሻሻል እንዲቻል በመተማ ወረዳ በ30 ሄክታር መሬት ላይ የምርምር ማዕከል በማቋቋም በተያዘው ዓመት የጥናት ስራ እየተካሄደ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

ማዕከሉ ለጥናት ስራው እንዲያግዘው ከሌሎች የበግ ዝርያዎች ጋር ያልተዳቀሉ ከ170 በላይ የጉምዝ በጎችን ከመተማና ከቋራ ወረዳዎች በማሰባሰብ  የዝርያ መረጣና ማሻሻል ስራውን ቀጥሏል፡፡

የጉምዝ በግ ዝርያ የደጋ በጎች ለእርድ ከሚደርሱበት የአንድ ዓመት ጊዜ በሰባት ወር ቀድሞ ለእርድ መድረሱ ልዩ ያደርገዋል"ብለዋል፡፡

በስጋ ምርታማነትም ቢሆን የደጋ በጎች አማካኝ የስጋ ምርታቸው 17 ኪሎ ግራም ሲሆን ከአንድ የጉምዝ በግ እስከ 27 ኪሎ ግራም የስጋ ምርት ማግኘት ያስችላል፡፡

በአሁኑ ወቅት ሩጣና ከሚባለው የሱዳን በግ ዝርያ ጋር በመዳቀል ለአደጋ ተጋልጦ ይገኛል፡፡

ማዕከሉ ዝርያውን ከመጥፋት ለመታደግ የመጠበቅና የማሻሻል ስራ ተቀዳሚ ዓላማው አድርጎ እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡

እንደ ተመራማሪው ገለፃ ማዕከሉ ያልተዳቀሉ ንጹህ ዝርያዎችን መርጦ በማራባት በአካባቢው በበግ እርባታ ፕሮጀክት ለታቀፉ አርሶ አደሮች ለማቅረብ አቅዷል፡፡

አርሶ አደሮቹ በጎቹን አድልበው ለሀገር ውስጥም ሆነ ለውጪ ገበያ በማቅረብ እራሳቸውን ከመጥቀም ባለፈ በዘርፉ የሀገሪቱን የወጭ ንግድ ለማሳደግ ትኩረት መሰጠቱን  ተመራማሪው ተናግረዋል፡፡

የመተማ ወረዳ የእንስሳት ሀብት ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዶክተር ቴዎድሮስ አደም በበኩላቸው "ማዕከሉ በወረዳው የጀመረው የጉምዝ በግ ዝርያ ጥበቃና ማሻሻል ስራ የሚደገፍና የሚበረታታ ነው" ብለዋል፡፡

የጉምዝ በግ ከሌሎች ዝርያዎች በስጋ ምርታማነቱና ፈጥኖ ለእርድ የሚደርስ በመሆኑ በወረዳው እንስሳት አርቢዎች ዘንድ ከፍተኛ ተፈላጊነት እንዳለው ተናግረዋል፡፡

የጉምዝ በግ አሁን ላይ ቁጥሩ ከ50ሺህ የማይበልጥ ሲሆን በዞኑ በመተማ፣ በቋራ፣ በምዕራብ አርማጭሆና ጠገዴ ወረዳዎች በሚገኙ ቆላማ አካባቢዎች እንሚኖር ከማዕከሉ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ