አርዕስተ ዜና
×

Warning

JUser: :_load: Unable to load user with ID: 452

በድሬደዋ በካይዘን አሰራር ከ46 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ከብክነት ማዳን ተቻለ

04 Oct 2017
2234 times

ድሬደዋ መስከረም 24/2010 ድሬደዋ 24/2010 በድሬዳዋ አስተዳደር የካይዘን አሰራር የተጠቀሙ ተቋማት  ከ46 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ከብክነት ማዳን መቻሉን የአስተዳደሩ ስራ አመራርና የካይዘን ኢንስቲትዩት ገለጸ፡፡

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር  አቶ አወቀ ለገሰ ለኢዜአ እንዳሉት  ሀብትና ንብረቱን ማዳን የቻሉት   ባለፉት አምስት ዓመታት የካይዘን ፍልስፍና አሰራርን ተግባራዊ  ያደረጉ 20 ያህል ተቋማት ናቸው ፡፡

ከተቋማቱም መካከል  ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ የዘርፍ መስሪያ ቤቶችና ኢንዱስትሪዎች ይገኙበታል፡፡

የካይዘን ፍልስፍናን ከመሠረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥና ከውጤት ተኮር የለውጥ መሣሪያዎች ጋር ተግባራዊ በማድረግ  አለጥቅም በየመጋዘኑ ተከማችተው ለብክነት ተዳርገው  የነበሩ ልዩ ልዩ ቁሳቁሶች በመሰብሰብ ከ33 ሚሊዮን ብር በላይ በጨረታ መሸጥ ተችሏል፡፡

በተለይም  በርካታ ነዋሪዎች በሚገለገሉባቸው የዘርፍ መስሪያ ቤቶች  የነበረውን የተዝረከረከ የመረጃ አያያዝ ስርዓት  በማስያዝ  የተቀላጠፈ  አገልግሎት ለመስጠት ማገዙን   ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

" አምና በአስር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችና ሌሎች ተቋማት ካይዘን መተግበሩ ከ13 ሚሊዮን ብር በላይ ሃብት ከብክነት ማዳን ተችሏል" ብለዋል፡፡

በተያዘው  በጀት ዓመትም እነዚህን ውጤቶች የመጠበቅና የማስፋት እንዲሁም ፍልስፍናው ይበልጥ በኢንዱስትሪዎች ውስጥ በማጠናከር  በድሬዳዋ ጥራት ያለው ምርት ለገበያ የሚያቀርቡ አምራቾችን ለመፍጠር  በቅንጅት እንደሚሰራ ነው አቶ አወቀ ያመለከቱት፡፡

" በተቋማችን አለአገልግሎት  የተቀመጡና የባከኑ በርካታ የውሃ ሞተሮችና የውሃ ቱቦዎች ተገኝተዋል" ያሉት ደግሞ  በአስተዳደሩ የውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን የንብረትና አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት ባለቤት አቶ ማስረሻ ታደሰ ናቸው፡፡

የካይዘን አሰራር ተግባራዊ በማድረጋቸው ይህንን በማስተካከል  ፈጣን አገልግሎት መስጠት እንዳስቻላቸው ጠቁመው አሰራሩ በሁሉም ተቋማት ቢስፋፋ ኪራይ ሰብሳቢዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እንደሚያግዝም ጠቁመዋል፡፡

በአስተዳደሩ የግብርና ጽህፈት ቤት የለውጥና የመልካም አስተዳደር ባለሙያ አቶ መልካሙ ጋሻው በበኩላቸው  የካይዘን አሰራር ተግባራዊ በማድረግ  ከሁለት  ሚሊዮን ብር በላይ  የሚገመት ሃብት ከብክነት ማዳን መቻሉን ገልጸዋል፡፡

" ፍልስፍናው አኗኗርን ፣አሰራርን ይቀይራል፣ ምቹ የሥራ አካባቢን በመፍጠር የተሻለ ሥራ ለመስራት ያስችላል"ብለዋል፡፡

እነዚህን ውጤቶች ለማስፋት የሚያግዝ ውይይት ከትናንት በስቲያ በተካሂደበት ወቅት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ኢብራሂም ዑስማን ካይዘን በሁሉም ሠራተኛና  ተቋማት ሰርፆ ውጤታማነቱን ለማጎልበት  አስተዳደሩ በትኩረት  እንደሚሰራ አስታውቀዋል፡፡

 

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ