አርዕስተ ዜና
×

Warning

JUser: :_load: Unable to load user with ID: 452

አየር መንገዱ አሰራሩን ሙሉ ለሙሉ ወደ ዲጂታል ቴክኖሎጂ ቀየረ Featured

29 Sep 2017
1773 times

አዲስ አበባ መስከረም 19/2010 የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሙሉ ለሙሉ አሰራሩን ከወረቀት ወደ ዲጂታል ቴክኖሎጂ መቀየሩን አስታወቀ።

አሰራሩ ከዚህ ቀደም በወረቀት ይሰሩ የነበሩ ሥራዎችን በኮምፒታር በመጠቀምና በኔትወርክ በማያያዝ የተለያዩ የሥራ ሂደቶችን ያለምንም ወረቀት በዲጂታል ለመሥራት የሚያስችል ነው።

አዲሱ አሰራር  በሰራተኞች ላይ ምንም ዓይነት ተፅዕኖ የማያሳድር፣ ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት የሚያስችልና ወጪ ቆጣቢ ነው ተብሏል።

የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም እንደገለጹት ድርጅቱ የዲጂታል አሰራር ከጀመረ ከ10 ዓመታት በላይ ያስቆጠረ ቢሆንም ፣ ሙሉ በሙሉ ወደ ተግባር አልተገባም ነበር።

ከዚህ በኋላ ድርጅቱ አጠቃላይ አሰራሮቹን ሙሉ በሙሉ ከወረቀት በፀዳ መልኩ የዲጂታል ቴክኖሎጂን እንደሚከተል ገልጸዋል።

የአውሮፕላን ጥገና፣ የበረራና የንግድ አገልግሎቶች፣ የፋይናንስ ሥርዓት ፣ የሰው ኃብት አስተዳድር ፣ የኦንላይን ትምህርት ፣ አመራር ውሳኔዎች፣ እና ሌሎችም የሥራ ዓይነቶች በአዲሱ አሰራር መሰረት ገቢራዊ ይደረጋል።

አዲሱ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አሰራር አየር መንገዱን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆን ከማድረግ ባለፈ ፤ ደንበኞች ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላቸዋልም ብለዋል።

ከዚህ ቀደም በከፊል የኤሌክትሮኒክ ዲጂታል አገልግሎት የጀመረው አየር መንገዱ ፤ ሙሉ በሙሉ ዲጂታል በሚጀምርበት ጊዜ የክፍያ ፣ ግዥና የመሳሰሉት አገልግሎቶች በዚህ አሰራር ውስጥ ያልፋሉ ነው ያሉት።

ቴክኖሎጂው በሳይበር ጥቃት አደጋ ላይ እንዳይወድቅ ምን ቅድመ ዝግጅት ተደርጓል? ለሚለው ጥያቄ፤ "ድርጅቱ ዓለም ባፈራው ቴክኖሊሎጂ በመታገዝ ጥቃቱን ከመከላከል ባለፈ ፤ ሰው ሰራሽም ሆነ የተፈጥሮ አደጋ ቢያጋጥም ወዲያውኑ የሚተካ ማሽን ተዘጋጅቷል" ብለዋል።

12 ሺህ ሠራተኞች ያሉት የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ በአምስት አህጉሮች በሚገኙ 100 ዓለም አቀፍና በ19 የአገር ውስጥ መዳረሻዎች፣ በዓመት ከ8 ነጥብ 8 ሚሊዮን በላይ ለሆኑ ተጓዦች የበረራ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።  

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ