አርዕስተ ዜና

ማተሚያ ድርጅቱ ምስጥራዊ ህትመቶችን ለማጠናከር የሚያስችለውን ቴክኖሎጂ ስራ ላይ ሊያውል ነው Featured

07 Sep 2017
2514 times

አዲስ አበባ ጳጉሜ 2/2009 ብርሃንና ሠላም ማተሚያ ድርጅት ምስጢራዊ ህትመቶችን ለማጠናከር የሚያስችለውን አዲስ ቴክኖሎጂ ስራ ላይ ሊያውል እንደሆነ አስታወቀ።

ድርጅቱ መቀመጫውን ጀርመን ሀገር ባረገው ከሙልባወር ድርጅት እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ቴክኖሎጂው በሚኖረው ፋይዳ ላይ ተወያይቷል፡፡

የብርሃንና ሠላም ማተሚያ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተካ አባዲ በዚሁ ጊዜ እንደተናገሩት የምስጢራዊ ህትመት ጥንቃቄዎችን ወደ ላቀ ደረጃ ማሳደግ ይገባል።

በመሆኑም ከተለያዩ ሀገሮች ልምድ በመቅሰም ዓለም የደረሰበት የምስጢራዊ ህትመት ቴክኖሎጂ ተግባራዊ መደረግ አለበት ብለዋል።

ድርጅቱ ህትመት ለሚያቀርብላቸው ተቋማት ስለ አዲሱ ቴክኖሎጂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው እና ተመራጭ እንዲያደርጉት የተለያዩ ተግባራትን ያከናውናል ብለዋል ።

አዲሱ ቴክኖሎጂ በሚቀጥሉት ስምንት ወራት ውስጥ ወደ ስራ እንደሚገባ ነው ያስታወቁት አቶ ተካ።

በሃገሪቱ ያለውን የሀሰተኛ ማስረጃዎች መበራከት ችግር ለመቅረፍ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየሰራ እንደሆነም ነው አቶ ተካ የጠቆሙት።

የሙልባወር ድርጅት አማካሪ ዶክተር ጳውሎስ ጎርፉ  እንደገለጹት ዓለም በአሁኑ ወቅት እየተጠቀመበት ያለው የምስጢራዊ ህትመት ቴክኖሎጂ “የፕላስቲክ ካርድ” ሲሆን ብርሃንና ሠላም ማተሚያ ድርጅት የዚሁ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ መሆን አለበት።

የሙልባወር ድርጅት ለተለያዩ ሀገራት የህትመት ድርጅቶች የህትመት ሲስተም በመዘርጋት እና ዘመናዊ የህትመት ማሽኖችን በማቅረብ እንደሚታወቅ ዶክተር ጳውሎስ ጠቁመዋል። 

ብርሃንና ሠላም ማተሚያ ድርጅት ምስጢራዊ ህትመት  ከጀመረ 45 ዓመታትን አስቆጥሯል።

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ