አርዕስተ ዜና
×

Warning

JUser: :_load: Unable to load user with ID: 452

በአማራ ክልል ተምችን ለመከላከል የሚያስችል ምርምር እየተካሄደ ነው

07 Sep 2017
2489 times

ባህር ዳር ጳጉሜ 2/2009 በአማራ ክልል የተከሰተውን ተምች በዘላቂነት ለመከላከል የሚያስችል የምርምር ስራ እያካሄደ መሆኑን የክልሉ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

በኢንስቲትዩቱ የተባይ ነፍሳት ተመራማሪ አቶ ምንተስኖት ወርቁ እንዳስታወቁት ተቋሙ ከሐምሌ 8 ቀን 2009 ጀምሮ በላብራቶሪ ተምቹን መግደል የሚችል ኬሚካል ለማግኘት በምርምር የመለየት ስራ ሲያከናውን ቆይቷል።

የተመረጡ 13 የፀረ-ሰብል ተባይ መከላከያ ኬሚካሎችን በሀገር ደረጃ በማሰባሰብ እስካሁን በላብራቶሪ ባከናወነው የምርምር ስራ ተምቹን በ48 ሰዓት ውስጥ መቶ በመቶ መግደል የሚችሉ አምስት ኬሚካሎችን መለየት ተችሏል።

ኬሚካሎቹም በሰው ጤንነት ላይ ጉዳት የማያደርሱና አካባቢውን የማይበክሉ መሆናቸው የተረጋገጠላቸው እንደሆኑም አስረድተዋል።

ተምቹ የትኛውን ሰብል ለይቶ እንደሚያጠቃ ለመለየትም በምርምር ቦታ በበቀለ የበቆሎ፣ ስንዴ፣ ገብስ፣ ዳጉሳና ጤፍ ሰብሎች ላይ  ምርምር ሲደረግ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡

በተከናወነው የምርምር ስራም ተምቹ ሁሉንም ሰብሎች ሳይመርጥ እንደሚያጠቃ ተረጋግጧል፡፡

በክልሉ ተምቹ ከታየበት ካለፈው ግንቦት ወር ጀምሮ እስካሁን 120 ሺህ ሄክታር የበቆሎ ሰብልን የወረረ ሲሆን ከዚህ ውስጥም 96 በመቶውን በኬሚካልና በባህላዊ መንገድ መከላከል መቻሉን የክልሉ ግብርና ቢሮ መግለጹ ይታወሳል።

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ