አርዕስተ ዜና

''አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በማላመድ የተጀመረውን ልማት ለማፋጠን የበኩላችንን ድርሻ እንወጣለን'' -የኮሌጅ ተመራቂዎች

02 Sep 2017
2615 times

አዲስ አበባ ነሐሴ 27/2009 ''አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በማላመድ የተጀመረውን ልማት ለማፋጠን የበኩላችንን ኃላፊነት እንወጣለን'' ሲሉ የኦርቢት ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኮሌጅ ተመራቂዎች ገለጹ።

ኮሌጁ ዛሬ ካስመረቃቸው ተማሪዎች ከአካውንቲግ የትምህርት ክፍል 96 ነጥብ 5 በማምጣት ተሸላሚ የሆነው ተማሪ ኤሊያስ ውዴ ያገኘሁትን እውቀት ወደ ተግባር ለመቀየር ተዘጋጅቻለሁ ብሏል።

ከኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ትምህርት ዘርፍ 94 ነጥብ 5 ያመጣው ተማሪ ነቢል ሙሰማ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች በአገሪቱ እንዲስፋፉና ተግባር ላይ እንዲውሉ ለማድረግ የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣ ተናግሯል።

አዳዲስ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ያልሆኑ የአገሪቱ አካባቢዎችን ተጠቃሚ በማድረግ ረገድም በሙያው ለማገልገል ቁርጠኛ እንደሆነም ገልጿል። ነው የሚገልጸው።

በተማረችው ሙያ መስክ ኃላፊነቷን በታማኝነትና በአግባቡ በመወጣት አገሪቱ የጀመረችውን የልማት ጉዞ ከግብ ለማድረስ የበኩሏን ጥረት እንደምታደርግ የገለጸችው ደግሞ በሴክሬቴሪያል ሳይንስና ኦፊስ ማኔጅመንት የተመረቀችው ዮዲት አጥናፉ ናት።

ተመራቂ ዮዲት 95 ነጥብ 5 ውጤት በማስመዝገብ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆናለች።

የኮሌጁ ፕሬዝዳንት ኢንጅነር ዘርአይ ገዛኸኝ የቴክኖሎጂ ምጥቀት ለአገር እድገት ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ይገልጻሉ።

በአገሪቱ ፈጣን ልማትና ዘላቂ እድገትን ለማረጋገጥ የኮሌጁ ተመራቂዎች በሚሰማሩበት የሙያ መስክ ጠንክረው መስራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

ኮሌጁ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ በአካውንቲንግ፣ በሴክሬቴሪያል ሳይንስ ፡ በኦፊስ ማኔጅመንትና በማርኬቲግ ለ13ኛ ጊዜ በቴክኒክና ሙያ ደረጃ በቀንና በማታ መርሃ ግብር ያሰለጠናቸውን 630 ተማሪዎች አስመርቋል።

በምረቃው ስነ ስርዓት ላይ ኮሌጁ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የዋንጫና የወርቅ ሜዳሊያ ሽልማት አበርክቶላቸዋል።
-

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ