አርዕስተ ዜና
×

Warning

JUser: :_load: Unable to load user with ID: 452

በጋምቤላ ክልል የተፈጥሮ ሀብት ልማቱን በምርምር ማገዝ ይገባል....አቶ ጋትሉዋክ ቱት

12 Aug 2017
1688 times

ጋምቤላ ነሀሴ 6/2009 በጋምቤላ ክልል ለግብርና ልማት የሚውለውን  ሰፊ  የተፈጥሮ  ሀብት  በምርምር በማገዝ የህዝቡን ተጠቀሚነት ለማሳደግ የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጠንክረው ሊሰሩ እንደሚገባ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ጋትሉዋክ ቱት አስገነዘቡ።

"የግብርና ቴክኖሎጂዎች ተጠቃሚነትና የምርምር ተደራሽነትን የማስፋት ፕሮጀክት" አስመልክቶ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በጋምቤላ ከተማ ውይይት እያደረጉ ነው።

ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ጋትሉዋክ ቱት እንደገለጹት በክልሉ ያለውን ሰፊ የእንስሳት፣ የውሃና  የመሬት ሀብት በምርምር በማገዝ ህዝቡን ይበልጥ ተጠቃሚ ማድረግ  ከዘርፉ ባለድርሻ አካላት ብዙ ይጠበቃል ።

በክልሉ ሰፊና ያልተነካ የተፈጥሮ ሀብት ቢኖርም በምርምር ታግዞ ማልማት ባለመቻሉ ሕዝቡ በሚፈለገው ደረጃ ተጠቀሚ ሳይሆን መቆየቱን ተናግረዋል።

በተለይ በሀገሪቱ እየተመዘገበ ላለው ባለሁለት አሀዝ የኢኮኖሚ እድገት የግብርናው ዘርፍ ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ "ዘርፉን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግና ቀጣይነት ያለው እድገት ለማስመዝገብ የምርምር ሥራዎች ሊጠናከሩ ይገባል"።

የክልሉ ግብርና ምርምር ተቋም በሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች ያሉትን ተሞክሮችን በመውሰድና ከፌደራል ግብርና ምርምር ተቋም የሚሰጠውን ድጋፍ በመጠቀም መስራት ይኖርበታል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ምክር ቤት ሴክሬታሪያትና የፌደራል ግብርና ምርምር ተቋም በክልሉ ላሉ አርሶና ከፊል አርብቶአደሮች የተሻሻሉ የግብርና አሰራሮችን ተደራሽ ለማደረግ በሚሰሩ ሥራዎች ድጋፋቸውን እንዲያጠናክሩ ጠይቀዋል።

የክልሉ ግብርና ምርምር ተቋም ዋና ዳሬክተር አቶ ኮንግ ጆክ በበኩላቸው "በክልሉ የተሻሻሉ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በማፈለቅ  ምርታማነትን ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት የአጋር አካላት ድጋፍ ሊጠናከር ይገባል" ብለዋል።

ከመድረኩ ተሳታፊዎች መካከል ዶክተር ኡማን አሙሉ በሰጡት አስተያየት የክልሉ የተፈጥሮ ሀብት በቴክኖሎጂ ታግዞ ቢለማ ለክልሉ ብቻ ሳይሆን ለሀገር የሚተርፍ ምርት ማግኝት እንደሚቻል ተናግረዋል።

እንደ ዶክተር ኡማን ገለጻ በክልሉ ያለውን የምርምር ተቋም አቅም በማሳደግ የተሻሻሉ የግብርና ቴከኖሎጂዎችን ለማፍለቅ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ያስፈልጋል።

በጋምቤላ ከተማ ትናንት በተጀመረው የውይይት መድረክ በግብርና ምርምር ሥራዎች ላይ የመነሻ ጹሁፎች ቀርበው ውይይት እየተደረገባቸው ይገኛል፡፡

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ