አርዕስተ ዜና
×

Warning

JUser: :_load: Unable to load user with ID: 452

ምድራችንን ለመታደግ የአመጋገብና የግብርናውን ስርዓት መቀየር ያስፈልጋል - ጥናት

19 Jun 2017
2311 times

ሰኔ 12/2009 የዓለም ህዝብ አመጋገቡንና የግብርና ስርአዓቱን መቀየር ካልቻለ መሬት ቁጥሩ እየጨመረ የመጣውን የዓለም ህዝብ ማስተናገድ እንደሚሳናት የሜኔሶታ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ጥናት ይፋ አደረገ፡፡

የተመራማሪዎቹ ጥናት እንደሚጠቁመው የግብርና ምርቶችን ግብዓት ተጠቅመን ከማምረት በተፈጠሮኣዊ መንገድ ወደ ማምረት  ማሸጋገሩ ብቻውን በመሬት ላይ የሚደርሰውን ተጽእኖ አያስቀረውም፡፡

ምግብን በማምረት ሂደት ጥቅም ላይ የሚውሉ ግብአቶች፣ የመሬትና የሃይል አጠቃቀም፣ የበካይ ጋዝ ልቀትና ጥቅም ላይ የሚውሉ  ኬሚካሎች ከውሃ ጋር በመቀላቀል በአከባቢ ላይ የሚያስከትሉት ስነህይወታዊ ጉዳትም በጥናቱ ተዳስሰዋል።

ምንም እንኳን ውጤት ተኮር ግብርና በአካባቢ ላይ የሚያስከትለው ተጽዕኖ አነስተኛ እንደሆነ ቢታመንም በጥናቱ የተደረሰበት እውነታ ግን የተቀላቀለ መሆኑን ሚካኤል ክላርክ የተባሉ ተመራማሪ ተናግረዋል፡፡

በተፈጥሮአዊ መንገድ ማምረት አነስተኛ ኃይል ቢጠይቅም ሰፊ መሬት ይፈልጋል፡፡ ይህ ደግሞ ከበካይ ጋዝ ልቀት ጋር በተያያዘ የሚኖረው ፋይዳ አነስተኛ ከመሆኑም ባሻገር በምርት ሂደት አሲዳማነትንና በውሃማ አካላት ላይ ከልክ ያለፈ ንጥረ ነገር እንዲከማች በማድረግ ስነ ህይወታዊ ምህዳሩን ያዛባዋል፡፡

ሳር የሚመገቡ ከብቶች ብዙ መሬትን ይጠቀማሉ በካይ ጋዝንም በመልቀቅ ጥራጥሬ ከሚመገቡ ይልቅ ከፍተኛ ድርሻ አላቸው ነው የሚሉት አጥኚዎቹ፡፡      

የከብት፣ የፍየልና የበግ ሥጋ መጠቀም ከሌሎች እንስሳት ሥጋ  በላይ  በአካባቢ ላይ ከሶስት እስከ አስር እጥፍ ጉዳት እንደሚያስከትል የጠቀሱት ተመራማሪው በአንፃሩ የአሳማ፣ የዶሮ  እና የአሳ ስጋ አካባቢንና ጤናን በመጠበቅ በጎ ተፅእኖ እንዳለውም በጥናቱ ተደርሶበታል፡፡

በአመጋገብና በግብርና ስርዓቱ ላይ ማስተካከያ እስካልተደረገ ድረስ ዓለማችን ራሷን ለመመገብ ማዳበሪያና ጸረ ተባይ ኬሚካሎችን ጨምሮ የመሬት ምንጣሮና መሰል  አማራጮችን በብዛት ጥቅም ላይ ልታውል እንደምትችል አስጠንቅቀዋል፡፡

የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል የየሀገራቱ መንግስታት ፓሊሲዎችና በመስኩ የሚሰጠው ትምህርት ለውጦቹን ለማምጣት የሚያበረታቱ መሆን እንዳለባቸውም ተመራማሪዎቹ  ጠቁመዋል፡፡

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ