አርዕስተ ዜና

የኮንስትራክሽን ዘርፉን የሚያስተሳስር የተቀናጀ ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ስርዓት ሊተገበር ነው Featured

15 May 2017
2982 times

አዲስ አበባ ሚያዝያ 7/2009 የኮንስትራክሽን ዘርፉን በአገር አቀፍ ደረጃ የሚያስተሳስር የተቀናጀ ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ስርዓት ተግባራዊ ሊደረግ መሆኑን የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ ከሁሉም ክልሎችና ከሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ከተውጣጡ አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር የተቀናጀ ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ስርዓት ልማት ምንነትና ዘመናዊ መረጃ ልውውጥ ዙሪያ ለሁለት ቀናት ያዘጋጀው ስልጠና ዛሬ ተጀምሯል።

ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ገብረመስቀል ጫላ እንደተናገሩት በዘርፉ የሚታዩትን የፕሮጀክት መጓተት፣ የኪራይ ሰብሳቢነት፣ የሀሰተኛ ሰነድና ሌሎችም ችግሮች ማቃለል የሚያስችለው ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ስርዓት ጥናት ተገባዷል።

ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ሶፍት ዌሩ የባለሙያዎችን፣ የስራ ተቋራጮችንና የግንባታ ስራ መሳሪያዎችን ምዝገባ አጣምሮ የሚይዝ እንደሆነም ጠቁመዋል።

በሚኒስቴሩ የዳታ ቤዝ ልማት ዳይሬክተር አቶ በድሩ ከድር በበኩላቸው አሰራሩ የባለሙያ፣ የስራ ተቋራጮችና ኮንስትራክሽን መሳሪያዎችን የምዝገባ አገልግሎት አሰጣጥ ቀልጣፋና ዘመናዊ እንደሚያደርገው ተናግረዋል። 

ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ስርዓቱ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተመርቀው የሚወጡትን ባለሙያዎች መረጃም እንደሚይዝ የተናገሩት አቶ በድሩ በቅድሚያ በፌዴራል ደረጃ ተግባራዊ ከተደረገ በኋላ ከክልሎች ጋር የሚተሳሰር መሆኑንም ነው የገለፁት።

የመረጃ አያያዝ ስርዓት ባለመኖሩ የፕሮጀክቶች ግንባታ መጓተት፣ ኪራይ ሰብሳቢነት፣ አንድን ፕሮጀክት ሳይጨርሱ ሌሎችን መያዝ፣ ሐሰተኛ የሰነድ ማስረጃና ሌሎችም ችግሮች ዘርፉን እየጎዱት እንደሆነም ተገልጿል።

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ