አርዕስተ ዜና

ራንሰምዌር በተሰኘ የሳይበር ጥቃት በ99 ሃገራት የሚገኙ ኮምፒተሮች ጉዳት ደርሶባቸዋል

13 May 2017
2801 times

ግንቦት 5/2009 በአሜሪካን ብሄራዊ ደህንነት ኤጀንሲ እንደተፈጠረ በሚታመነው መሳሪያ ሰፋ ያለ የሳይበር ጥቃት በብዙ የአለማችን ድርጅቶች ላይ መሰንዘሩን ቢቢሲ ዘገበ፡፡  

ብዙ ቦታ የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ ኮምፒተሮችም የ300 ዶላር ኦን ላየን ክፍያ እንዲፈፀምላቸው በሚጠይቁ ፕሮግራሞች ተዘግተዋል፡፡ 

በሚያዚያ ወር “ዘ ሻዶው ብሮከር” የተሰኘው የኮምፒውተር ጠላፊ የሳይበር ጥቃት የሚያደርሰውን መሳሪያ ሰርቆ ኦንላይን እንዳሰራጨው አሳውቆ ነበር ፡፡

ማይክሮ ሶፍት ባሳለፍነው መጋቢት ወር ተጋላጭ ለሆኑ ኮምፒተሮች የጥገና ፕሮግራሞችን ቢለቅም ብዙ ሲስተሞች እራሳቸውን “አፕዴት” ማድረግ አልቻሉም ፡፡

 

ጥቃቱ ያስከተለው ጉዳት

የሳይበር ጥቃቱ በ99 ሃገራት መድረሱ የታወቀ ሲሆን ከነዚህም መካከል እንግሊዝ፣አሜሪካን፣ቻይና፣ራሺያ፣ስፔን እና ጣልያን ይገኙባቸዋል፡፡

የሳይበር ደህንነት ላይ የሚሰራው አቫስት 75 ሺህ “ዋናክራይ” እና ሌላ ስም ያላቸው  የራንሰምዌር ጥቃቶች  በአለም ዙሪያ እንዳሉ ተናግሯል፡፡ 

ብዙ አጥኚዎች እንዳሉት ክስተቱ እርስ በርሱ የተያያዘ ቢሆንም ነገር ግን አንድ አካልን ለማጥቃት የተቀናጀ እንዳልሆነ ገልፀዋል፡፡

የጥቃት አድራሺዎቹ ኦን ላየን በሚከፈል ገንዘብ እየተጥለቀለቁ መሆኑም ታውቋል፡፡

 

የጉዳቱ ሰለባዎች

 

በእንግሊዝና ስኮትላንድ የሚገኘው ብሄራዊ የጤና አገልግሎት “ዋናክራይ” የተሰኘውን ፕሮግራም በሰራተኞቹ አማካኝነት ሼር በመደረጉ አስከፊው ጥቃት ደርሶበታል፡፡

ሆስፒታሎችና ቀዶ ጥገና የሚሰሩ ሃኪሞችም በሽተኞችን እየመለሱና ቀጠሮ እየሰረዙ መሆኑ ታውቋል፡፡ በተቋሙ የሚሰራ ባለሙያ እንደገለፀው በጥቃቱ በሽተኞች ችግር ውስጥ ወድቀዋል ፡፡  

የዘርፉ ተመራማሪዎች ባስቀመጡት ግምት የአሜሪካን ብሄራዊ ደህንነት ኤጀንሲ ፕሮግራሙን የማይክሮሶፍት ሲስተም ድክመትን ለማወቅ የሰራው ቢሆንም  በዘራፊዎች እጅ በመውደቁ ችግሩ እንደተከሰተ ገልፀዋል ፡፡  

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ