አርዕስተ ዜና

የኮሪያ የጉምሩክ ክሊራንስ ስርዓት ወደኢትዮጰያ ለማስገባት ስምምነት ተደረሰ

13 Mar 2017
1297 times

መጋቢት 4/2009 የደቡብ ኮሪያ የጉምሩክ ኤጀንሲ  የኤሌክትሮኒክ ጉምሩክ ክሊራንስ ስርኣትን ወደ ኢትዮጲያ  ለማስገባት የሚያስችለውን የ13 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት  ከኢትዮጲያ ጋር መፈራረሙን  ኮሪያ ሄራልድ ዘገበ፡፡  

በስምምነቱም ዩኒፓስ "UNI-PASS" የተሰኘው የደቡብ ኮሪያ የኤሌክትሮኒክ ጉምሩክ ክሊራንስ ስርአት እኤአ በ2020 በኢትዮጲያ እንደሚተገበር የኮሪያ ጉምሩክ አገልግሎት በመግለጫው አመልክቷል፡፡

ዩኒፓስ "UNI-PASS" በኮሪያ ጉምሩክ አገልግሎት የኤሌክትሮኒክ ክሊራንስ ፖርታል ሲስተም  መጠሪያ ነው፡፡

ደቡብ ኮሪያ  የጉምሩክ ክሊራንስ ሲስተሙን ከምታስገባባቸው 11 አገሮች ካሜሮን፣ ታንዛኒያና ኢትዮጲያ ተጠቅሰዋል ፡፡

እስከ አሁንም ሲስተሙን ወደ ተለያዩ ሀገራት በማስገባት የ348 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አግኝታበታለች፡፡

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ