አርዕስተ ዜና

በኢንተርኔት አማካኝነት አፍሪካን የሚያስተሳስረው 'ዶት አፍሪካ' ይፋ ሆነ Featured

10 Mar 2017
1564 times

አዲስ አበባ መጋቢት 1/2009 በኢንተርኔት አማካኝነት የአፍሪካን ማህበራዊና ባህላዊ ትስስር የማጎልበት ግብ ሰንቆ የሚንቀሳቀሰው 'ዶት አፍሪካ' በአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ይፋ ሆነ።

'ዶት አፍሪካ' በኢንተርኔት አማካኝነት አህጉሪቱን በአንድ ጥላ ስር ማስተሳሰር፣ የኢንተርኔት ንግድን ማቀላጠፍና የቴክኖሎጂ መሠረተ ልማት እንዲያድግ የሚሰራ ነው።

ለ'ዶት አፍሪካ' ምዝገባ እያካሄደ የሚገኘው ዜድ.ኤ.ሴንትራል ሬጂስተሪ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሞክጋቡዲ ሉኪ ማሲሌላ እንዳሉት 'ዶት አፍሪካ' በአህጉሪቱ ብቸኛው ዲጂታል መለያ ነው።

ድርጅቱ ካነገበው ዓላማ አንጻር በአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ይፋ መሆኑ ደግሞ ትልቅ ታሪካዊ ክስተት ነው ብለዋል።

ድርጅቱ በአፍሪካውያን ለአፍሪካውያን የተመሠረተ ሲሆን የአፍሪካውያን 'ኦን ላይን' መለያ እንዲኖራቸውና ምርት፣ አገልግሎትና መረጃ በቀላሉ እንዲለዋወጡ የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል።

''ሰዎች በህይወታቸው የስም መለያ እንዲኖራቸው ይፈልጋሉ፤ 'ዶት አፍሪካ'ም አፍሪካ እንደ አህጉር መለያ እንዲኖራት ያደርጋል ነው ያሉት።

አሁን ካሉት 1 ነጥብ 2 ቢሊዮን አፍሪካውያን መካከል 10 በመቶው ብቻ በ'ዶት አፍሪካ' አማካኝነት ቢተሳሰሩ ለአህጉሪቷ ትልቅ ስኬት ነው ይላሉ ስራ አስፈጻሚው።

በተጨማሪም 'ዶት አፍሪካ' የተወሰኑ የአፍሪካ አገር በቀል ቋንቋዎችንም በቴክኖሎጂው ዘርፍ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ለማስቻል ሀሳብ እንዳለው ገልጸዋል።

'ዶት አፍሪካ' እንደ አውሮጳውያን አቆጣጠር በ2012 ነው የተመሠረተው።

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ