አርዕስተ ዜና

በሳይንስ እና የጠፈር ቴክኖሎጂ ፈጠራ ፅሁፍ ውድድር የተሳተፈው ኢትዮጵያዊ ተማሪ አሸነፈ

17 Feb 2017
1922 times

የካቲት 10/2009 በልዩ የፓን አፍሪካን የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ውድድር የተሳተፉ ታዳጊ ተማሪዎች የዲ ኤስ ቲቪ ኢተልሳት የኮከቦች ሽልማት አግኝተዋል፡፡

በፈጠራ ፅሁፍ ዘርፍ ዳኞችን ያስደመመው ኢትዮጵያዊው ልኡል መስፍን ፓሪስ ተጉዞ የጠፈር ማዕከል የመጎብኘት እድል አግኝቷል፡፡

በፓሪስ ቆይታው ሳተላይትን ምኅዋር ላይ ለማሳረፍ ሮኬት ወደ ጠፈር እንዴት እንደሚላክ ይመለከታል፡፡

በፈጠራ ጽሁፍ ሁለተኛ የወጣው  ከታንዛንያ ዴቪድ ባዋና ነው፡፡

ዴቪድም በደቡብ አፍሪካ መልቲቾይስ እና ጆሀንስበርግ አቅራቢያ የሚገኘውን ብሄራዊ የጠፈር ኤጀንሲ የመጎብኘት እድል አግኝቷል፡፡

በፖስተር ዘርፍ አሸናፊ የሆነው ናይጄሪያዊው ኢማኑዌል ኦቼጄሌ ሆኗል፡፡

ኢማኑዌል ቴክኖሎጂ በመጠቀም የዘመኑ ፈተና የሆኑትን እንደ ሙቀት መጨመር መከላከል፤የብዝሀ ህይወት ጥበቃ እና አስተማማኝ የሀይል አቅርቦት ማበርከት የሚችል ፈጠራ አቅርቧል፡፡

ናይጄሪያዊው ኢማኑዌል ልክ እንደ ልኡል ፈረንሳይ ፓሪስ ተገኝቶ ሳተላይቶች እንዴት እንደሚሰሩ ለማየት በኢተልሳት ፋብሪካ ጉብኝት ያደርጋል፡፡

በዚሁ ዘርፍ ሁለተኛ የወጣው አቦክዌ ሌታሞ ከቦስትዋና ነው፡፡

ልዑል ከኢትዮጵያ እና ኢማኑዌል ከናይጄርያ በተወዳደሩበት ዘርፍ አንደኛ በመውጣታቸው የኢተልሳት ኮከቦች ዋንጫ ተሸላሚዎች ሆነዋል፡፡

ነግር ግን አራቱም የዲኤስ ቲቪ አጫጫን (installation) ዲሽ፤ቲቪ ገጠማ፤ፒቪአር ዲኮደር እና ነፃ የዲኤስቲቪ ቡኬት ትምህርት እድል ተሰቷቸዋል፡፡

በ6ኛው የፈጠራ ሀሳብ ፅሁፍ እና ፖስተር ዘርፍ በተደረገው ውድድር እድሜያቸው ከ14-19 የሆኑ ተማሪዎች ተሳትፈዋል፡፡

በዘንድሮው በውድድር ታዳጊ ተማሪዎች ያቀረቡት የፈጠራ ፅሁፍ እና ፖስተር ከዚህ ቀደም ከቀረበው አኳያ ሲታይ በትክክለኛነት፤በፈጠራ እና በሀሳቡ ባለቤትነት (originality) የተሻለ ሆኖ መገኘቱ ታውቋል፡፡

በውድድሩ ከ20 ሀገራት የተውጣጡ 1ሺህ ተማሪዎች የተካፈሉ ሲሆን ይህም ወደፊት አፍሪካ ለሚኖራት የሳተላይት ቴክኖሎጂ ተስፋ እንደሚሆኑ ያመላከተ ነው ተብሏል፡፡

የአውሮፓ ጠፈር ኤጀንሲ አማካሪ ካላውዲ ሀግኔሬ ”ይህ የአፍሪካ ታዳጊዎች ባለራዕይ ሀሳብ አህጉሪቱን በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ለማጠናከር ከፍተኛ ድርሻ አለው” ብለዋል፡፡

የቀጣዩ ውድድር ተሳታፊዎች በዚህ አመት መጨረሻ ይታወቃሉ ተብሏል፡፡

ምንጭ፡ቫንጋርድኤንጂአር

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ