አርዕስተ ዜና

የፌስቡክ ሀሰተኛ መረጃዎች አለምአቀፋዊነትን እየሸረሸሩት ነው- ዙከርበርግ

17 Feb 2017
2239 times

የካቲት 10/2009 የፌስ ቡክ መስራቹ ማርክ ዙከርበርግ አሁን ያለው የፌስቡክ አጠቃቀም አለምአቀፋዊነትን በሚፃረር መልኩ እየሄደ መሆኑ እንደሚያሳስበው ገለፀ፡፡

ዙከርበርግ ከቢቢሲ ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ የውሸት ዜናዎች፣ፅንፍ የወጡ አመለካከቶች እና የተሳሳቱ መረጃዎች ሰዎች “የጋራ ግንዛቤ” እንዳይኖራቸው መሰናክል እየሆኑ ነው ፡፡  

በመሆኑም በሀሰተኛ መረጃዎች ሰዎች ከአለም እድገት ተቋዳሽ እንዳይሆኑ ወደ ኋላ እየቀሩና በመሰላቸትም  እርስ በርስ ከተሳሰረው አለም እራሳቸውን እያገለሉ መሆኑን ጠቁሟል ፡፡

ይህንን አካሄድ ለመግታት ባቀረበው ጥሪም ሰዎች በመረጃዎቹ ተስፋ ከመቁረጥ ይልቅ ማህበራዊ ትስስሮሽን ለማሳደግ መስራት ይኖርባቸዋል ብሏል ፡፡ 

“ፌስ ቡክን በጀመርኩበት ወቅት አለምን በመረጃ መረብ ማገናኘቱ አወዛጋቢ አልነበረም፤ በዚህም አለም በየጊዜው እርስ በርስ እየተሳሰረች መጥታለች ህልማችንም ይሄ ነበር ” ያለው  ዙከርበርግ ”አሁን አልፎ አልፎ እየሆነ ያለው ነባራዊ ሁኔታ ግን ህልማችንን  አወዛጋቢ ሁኔታ ውስጥ ከቶታል “ብሏል፡፡

 

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ