አርዕስተ ዜና

ህንድ 104 ሳተላይቶችን በአንድ ተልዕኮ በማምጠቅ ክብረወሰን አስመዘገበች

15 Feb 2017
2119 times

የካቲት 8/2009 ህንድ በአንድ ተልዕኮ 104 ሳተላይቶችን በስኬት አምጥቃ ታሪክ በመስራቷ ከዚህ ቀደም በሩሲያ ተይዞ የነበረውን ክብረወሰን አሻሽላለች፡፡

በጠፈር ሳይንስ ትልቅ ስም ያላት ሩሲያ 37 ሳተላይቶችን በአንድ ተልዕኮ አምጥቃ ነበር፡፡

ሳተላይት የማመንጠቅ ተግባሩ የተከናወነው ሲሮሃሪኮታ በሚባለው የጠፈር ማዕከል ነው፡፡

አንዳንድ ተዛቢዎች እንደሚሉት ህንድ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ባለብዙ ቢሊዮን ዶላሩ የጠፈር ገበያ ዋንኛ ተዋናይ እየሆነች መምጣቷን ያሳያል ብለዋል፡፡
"ይህ ቀን ታሪክ የሰራንበት ታላቅ ቀን ነው" ሲሉ የፕሮጀክቱ ዳይሬክተር ጃያ ኩማር ገልፀዋል፡፡

የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በበኩላቸው በትዊተር ገፃቸው ለሳይንቲስቶች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ወደ ጠፈር ከተላኩት 104 ሳተላይቶች አብዛኞቹ የውጭ ሀገራት ናቸው፡፡

አሜሪካ የ96ቱ ሳተላይቶች ባለቤት ስትሆን ፤እስራኤል ፤ካዛኪስታን፤ የተባበሩት አረብ ኢሜሬትስ፤ስዊትዘርላንድ እና ኔዘርላንድ ሌሎች የውጭ ሀገራት ደንበኞች ናቸው፡፡

በቁጥር ላቅ የሚሉት ሳተላይቶች የምድር-ምስል የማሰስ አቅም ያላቸው ሲሆን የአሜሪካው ኩባንያ ፕላኔት ንብረት እንደሆኑ ተነግሯል፡፡

ከእነዚህ መካከል ከፍተኛ ጥራት ያለው ምስል መውሰድ የሚችለው የህንዱ ካርቶግራፊክ ሳተላይት ይገኝበታል፡፡

ህንድ በዚች ሳተላይት በክልሏ ያሉ የባላንጣዎቿን እንቅስቃሴ ለመከታተል ትጠቀምበታለች ተብሎ ተገምቷል፡፡

የቢቢሲው ዘጋቢ ሳንጆይ ማጁምደር ከዴልሂ አንደዘገበው ህንድ በጠፈር ፕሮግራሟ እውቅና ማግኘት ከመቻሏም በላይ ለሌሎች አለም አቀፍ የዘርፉ ተሳታፊዎች አስተማማኝ የሆነ ዝቅተኛ የወጪ አማራጭ እየሆነች ትገኛለች፡፡

የሀገሪቱ መንግስት ባለፉት ሁለት አስርት አመታት በፍጥነት እያደገ ለመጣው የጠፈር ፕሮግራም የበጀት ጭማሪም አድርጓል፡፡

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ