አርዕስተ ዜና
×

Warning

JUser: :_load: Unable to load user with ID: 444

የሚድሮክ ኢትዮጵያ ዓመታዊ የስፖርት ውድድር ተጠናቀቀ

22 May 2016
987 times

አዲስ አበባ ግንቦት 14/2008 የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያ ዓመታዊ የስፖርት ውድድር ተጠናቀቀ።

ለ13ኛ ጊዜ በተካሄደው ውድድር ላይ ተጋባዥ ተቋማትም የተሳተፉ ሲሆን ቴክኖ አቃቂ ኩባንያ አጠቃላይ አሸናፊ ሆኗል።

ከጥር 22 ቀን 2008 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ አምሰት ወራት በተለያዩ የስፖርት ዓይነት ሲካሄድ የነበረው ውድድር ዛሬ ተጠናቋል።

በውድድሩ ላይ 24 የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ እህት ኩባንያዎችና 11 ተጋባዥ ተቋማት 411 ወንድና 140 ሴት ስፖርተኞች ተካፋይ ሆነዋል።

ቴክኖ አቃቂና ከአዲስ ኢንተርናሽናል ከተር ጋር ዛሬ የእግር ኳስ የፍፃሜ ጨዋታ ተደርጓል።

በእግር ኳስ ለፍፃሜ የተጫወቱት ቴክኖ አቃቂ ከአዲስ ኢንተርናሽናል ከተር ሲሆን ቴክኖ አቃቂ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የዋንጫ ባለቤት ሆኗል።

ቴክኖ አቃቂ ከእግር ኳስ በተጨማሪ በሩጫና በሌሎች የስፖርት ዓይነቶች በማሸነፍ ውድድሩን በበላይነት አጠናቋል።

አትሌቲክስ፣መረብ ኳስ፣ሜዳ ቴኒስ፣ጠረጴዛ ቴኒስ፣ቼዝና ሌሎች የስፖርት ውድድሮችም ተካሄደዋል።

የሚድሮክ ኢትዮጵያ ሊቀመንበር ሼህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል አሙዲ የውድድሩ ዋና ዓላማ ሰራተኞች ስፖርታዊ እንቀስቃሴ በማዘውተር ጤንነታቸውን የሚጠብቁበትና የእርስ በርስ ግንኙነታቸውን እንዲያጠናክሩ ነው ብለዋል።

ውድድሩ ውጤታማና የታለመለትን ግብ የመታ ነው፤ ወደፊትም ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ ተናግረዋል።

የሚድሮክ ኢትዮጵያ ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር አረጋ ይርዳው በበኩላቸው ውድድሩ የሰራተኞችን የእርስ በርስ ግንኙነት ከማጠናከር ባለፈ የስራ ተነሳሽነት እንዲኖር ያግዛል ብለዋል።

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ