አርዕስተ ዜና

ቅዱስ ጊዮርጊስ በካፍ ሻምፒዮና በፎርፌ ወደ ቀጣዩ ዙር አለፈ

652 times

 አዲስ አበባ የካቲት 4/2010 የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ በካፍ ሻምፒዮና የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ በፎርፌ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፉን አረጋገጠ።

ዛሬ በ10 ሠዓት ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ የነበረበት የደቡብ ሱዳኑ ዋኡ ሳላም ክለብ በአዲስ አበባ ስታዲየም አልተገኘም።

በመሆኑም ቅዱስ ጊዮርጊስ በፎርፌ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፏል።

በአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን /ካፍ/ ሕግ መሰረት ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ሜዳው ገብቶ ለ15 ደቂቃ ልምምድ አድርጓል።

የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች በስታዲየም ተገኝተው ለቡድናቸው ድጋፍ ሰጥተዋል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ በቀጣዩ ዙር ከማዳጋስካሩ ቲ.ኤን.ኤ.ቲ.ኤስ እና ከኡጋንዳው ኬ.ቲ.ቲ.ኤ ክለብ አሸናፊ ጋር በመገናኘት በመጋቢት ወር ጨዋታውን ያደርጋል።

በሌላ ዜና በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ኢትዮጵያን የወከለው ወላይታ ድቻ ዛንዚባር ላይ ከአገሪቱ ክለብ ዚማሞታ ጋር ከቀኑ 10 ሠዓት ጀምሮ እየተጫወተ ሲሆን እስካሁን ሁለቱም ክለቦች ግብ አላስቆጠሩም።

Last modified on Monday, 12 February 2018 15:52
Rate this item
(0 votes)

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን