አርዕስተ ዜና

ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በፖላንድ የሎድዝ ማራቶንን አሸነፉ

266 times

አዲስ አበባ ሚያዝያ 8/2010 ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በፖላንድ ሎድዝ በወንዶች ማራቶንና ግማሽ ማራቶን ድልን ተቀዳጁ።

 በትናንትናው ዕለት ለ14ኛ ጊዜ በተካሄደው የሎድዝ ማራቶን አትሌት ታረቀኝ ዘውዱ ሁለት ሰዓት ከ19 ደቂቃ ከ41 ሴኮንድ በመግባት አሸንፏል።

 ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት አስማረ ወርቅነህ በሁለት ሰዓት ከ19 ደቂቃ ከ53 ሴኮንድ ሁለተኛ ሲሆን ኬንያዊው ሮጀርስ ኪፕቺርቺር ሁለት ሰዓት ከ21 ደቂቃ ከ50 ሴኮንድ በመግባት ሶስተኛ ደረጃን ይዟል።

 በወንዶች ማራቶን በሁለቱ ኢትዮጵያኖች መካከል እስከ መጨረሻው ሰዓት ድረስ ብርቱ ፉክክር እንደተደረገ ዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር በድረ-ገጹ አስፍሯል።

 በሴቶች ኬንያዊቷ ጃኔ ኪፕቶ፣ ፓላንዳውያኑ ናታሊ ሚየርዜክሊንና አግኒየስካ ፔልክዋኔሊስት ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ ይዘዋል።

 በሎድዝ የግማሽ ማራቶን ውድድር በወንዶች ኢትዮጵያዊው አትሌት ሁነኛው መስፍን አንድ ሰዓት ከሶስት ደቂቃ ከ17 ሴኮንድ በመግባት አሸናፊ ሆኗል።

 ኬንያዊው ሂላሪ ማዮ በአንድ ሰዓት ከሶስት ደቂቃ ከ41 ሴኮንድ ሁለተኛ ሲሆን ኢትዮጵያዊ አትሌት አማኑኤል ብርሃኔ አንድ ሰዓት ከሶስት ደቂቃ ከ52 ሴኮንድ በሆነ ሰዓት ሶስተኛ ደረጃን ይዟል።

 ሌላው ኢትዮጵያዊ አትሌት ዮናስ ያዕቆብ አራተኛ ደረጃን ይዟል።

 በሴቶች ፓላንዳውያኖቹ አግኒየስካ ጎርቴል፣ አና ዎጂክ እና ዶሮታ ጋፕስ ከአንድ እስከ ሶስት መግባት ውድድራቸውን አጠናቀዋል።

 በሌላ በኩል ዛሬ በሚካሄደው በአሜሪካ የቦስተን ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ይሳተፋሉ።

 በወንዶች ሌሊሳ ደሲሳ፣ ለሚ ብርሃኑና ታምራት ቶላ፤ በሴቶች ደግሞ አሰለፈች መርጊያ እንደሚወዳደሩ ይጠበቃል።

 

 

 

Rate this item
(0 votes)

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን