አርዕስተ ዜና

የምስራቅ ጎጃም ዞን ዓመታዊ የስፖርት ውድድር መካሄድ ጀመረ

12 Jan 2018
345 times

ደብረማርቆስ 4/2010 በምስራቅ ጎጃም ዞን ለመጪዎቹ አስር ቀናት የሚቆይ ዓመታዊ የልዩ ልዩ ስፖርት ውድድር መካሄድ ጀመረ።

ከጥር 2 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ እየተካደ በሚገኘው ውድድር  በ16 የስፖርት አይነቶች   1ሺህ 670 ወጣት ስፖርተኞች የሚሳተፉ ሲሆን ከነዚህ  መካከል 400 ሴቶች ናቸው ።

የዞኑ ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ መላኩ መሀሪ እንደገለፁት ውድድሩ እየተካሄደ ያለው ዞኑን ወክለው በክልል ደረጃ የሚሳተፉ  ስፖርተኞችን ለመምረጥ ነው 

ወጣቱን እርስ በእርስ በማገናኘት ወንድማማችነትን ማጠናከር እንዲሁም  ባህልንና ትውፊትን ማስተዋወቅ ሌላው የውድደሩ ዓላማ መሆኑን ተናግረዋል ።

ውድድሩ አዝናኝና ጤናማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣም መልዕክታቸውን  አስተላልፈዋል ።

 

 

 

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ