አርዕስተ ዜና

የፌዴሬሽኑ ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ለ3ኛ ጊዜ ተራዘመ

10 Jan 2018
327 times

አዲ አበባ ጥር 2/2010 የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን የፕሬዚዳንትና ስራ አስፈጻሚዎች ምርጫ ለሶስተኛ ጊዜ ተራዘመ።

የዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) እና የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (/ካፍ) የምርጫ ታዛቢዎች ቀደም ሲል ምርጫውን ለማካሄድ በተያዘው ቀን (ጥር 5 ቀን 2010) መገኘት እንደማይችሉ ማሳወቃቸው ለምርጫው መራዘም በምክንያትነት ተጠቅሷል።

ከምርጫው በኋላ ሊፈጠር የሚችለውን ችግር ለማስቀረት ከጥር 27 ቀን 2010 በኋላ  እንዲደረግ ፊፋ መጠየቁም ለምርጫው መራዘም ሌላው ተጠቃሽ ምክንያት ነው ተብሏል።

ይህን ተከትሎም ምርጫው ለሶስተኛ ጊዜ ወደ የካቲት 24 ቀን 2010 ዓ.ም መራዘሙን ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።

ለቀጣዩቹ አራት ዓመታት የኢትዮጵያን እግር ኳስ ፌዴሬሽን በፕሬዝዳንትነትና በስራ አስፈጻሚነት የሚመሩ አካላትን ምርጫ  ጥቅምት 30 ቀን 2010  በ10ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ነበር ይካሄዳል ተብሎ ቀጠሮ የተያዘለት።

ይሁን እንጂ  ከምርጫው ጋር ተያይዞ ይነሱ የነበሩ ችግሮችና ቅሬታዎች ስለነበሩ ወደ ታህሳስ አጋማሽ መራዘሙ ይታወቃል።

ከዚያ በኋላም ወደ ጥር 5 ቀን 2010 እንዲራዘም ተደርጎ ነበር። አሁን ደግሞ ወደ የካቲት 24 ቀን 2010 ዓ.ም መራዘሙና በተጠቀሰው ጊዜ በአፋር ክልል ሰመራ እንደሚካሄድ ተገልጿል።

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ