አርዕስተ ዜና

ፌዴሬሽኑ በሚቀጥለው ወር በተለያዩ ርቀቶችና በሜዳ ላይ ተግባራት ውድድሮችን ሊያካሂድ ነው

01 Jan 2018
403 times

አዲስ አበባ ታህሳስ 23/2010 የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በሚቀጥለው ወር በተለያዩ ርቀቶችና በሜዳ ላይ ተግባራት ውድድሮችን ሊያካሂድ ነው።

ውድድሩን ከመጪው ጥር 23 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ አምስት ቀናት የሚያካሄድ ሲሆን፤ በዚህም የአጭር ርቀት፣ የመካከለኛ ርቀትና የእርምጃ ውድድሮች እንዲሁም ውርወራና ዝላይ የሚባሉት የሜዳ ላይ የአትሌቲክስ ስፖርት ተግባራት ተካተዋል።

በፌዴሬሽኑ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ስለሺ ብስራት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደተናገሩት፤ የውድድሩ ዋና ዓላማ አሸናፊ የሚሆኑና አቅም ያላቸውን አትሌቶች በእጩነት በምመረጥ ለሁለት ተከታታይ ዓመታት ስልጠና ለመስጠትና በውድድሩ ዝቅተኛ ተሳትፎና ውጤት የሚታይባቸውን የአትሌቲክስ የስፖርት ዘርፍንም ለማጠናከር ታስቦ ነው።

በውድድሩ አሸናፊ ለሚሆኑ አትሌቶችም ከዚህ በፊት በተለየ መልኩ እንደየደረጃቸው "የገንዝብ ሽልማት ተዘጋጅቶላቸዋል" ብለዋል።

በዚህም መሰረት በቡድን የሴትና የወንድ የዱላ ቅብብል /ድብልቅ ሪሌ/ ውድድር አንደኛ የሚወጡ አምስት ሺ ብር፣ 2ኛ የሚወጡ 4 ሺ 500 ብር እንዲሁም ሶስተኛ ሆነው የሚያጠናቅቁ 3 ሺ ብር ሽልማት የሚያገኙ ይሆናል።

እንዲሁም በ4 በ 100 ሜትር ውድድር ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ የሚወጡ አትሌቶች ደግሞ 4 ሺ ብር፣ 3ሺ ብር እና 2ሺ ብር  እንደየቅደም ተከተላቸው ተሸላሚ ይሆናሉ።

ፌዴሬሽኑ በሌሎች ርቀቶችና የሜዳ ላይ አትሌቲክስ ስፖርቶች አሸናፊ ለሚሆኑም የገንዘብ ሽልማት እንዳዘጋጀላቸው ነው የገለጸው።

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ