አርዕስተ ዜና

ጅማ አባጅፋርና ጅማ አባቡና ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ

31 Dec 2017
471 times

ጅማ ታህሳስ 22/2010 በጅማ ከተማ ትናንት በተካሄዱ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግና የከፍተኛ ሊግ ጨዋታዎች የከተማው ክለቦች ጅማ አባቡናና ጅማ አባጅፋር ተጋጣሚዎቻቸውን በሰፊ የጎል ልዩነት አሸነፉ፡፡

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ትናንት ከቀኑ 7 ሰዓት ላይ ስልጤ ወራቤን የገጠመው ጅማ አባጅፋር አራት ለ አንድ በሆነ ውጤት አሸንፎ መውጣት ችሏል፡፡

ባለሜዳው ጅማ  አባቡና ጎል ማስቆጠር የጀመረው ጨዋታው በተጀመረ በአንደኛው ደቂቃ በቴዎድሮስ ታደሰ አማካኝነት ነበር ።

ብዙአየሁ እንዳሻው በ12ኛው፣ በ34ኛውና በ42ኛው ደቂቃዎች ባስቆጠራቸው ግቦች ሃትሪክ የሰራ ሲሆን የአባቡናን ቡድን የግብ ብዛት ወደ አራት ከፍ አድርጎታል ።

የስልጤ ወራቤ ቡድን በባዶ ከመሸነፍ ያዳነችውን ብቸኛ ግብ በ85ኛው ደቂቃ ያስቆጠረው ገብረመስቀል ዱባለ ነው ።

ጅማ አባቡና ማሸነፉን ተከትሎ ዛሬ ሌሎች ጨዋታዎች እስከሚካሄዱ ድረስ ከ6ኛ ደረጃ ወደ ሁለተኛ ደረጃ ከፍ ማለት ሲችል ተጋጣሚው ስልጤ ወራቤ ለጊዜው በነበረበት 5ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣል፡፡

ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ የተካሔደው ሁለተኛ ጨዋታ ደግሞ የአምና የከፍተኛ ሊግ የፍፃሜ ተፋላሚዎች የነበሩትና ተያይዘው ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የተቀላቀሉት ጅማ አባጅፋርና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን ያገናኘ ነበር ።

እኩል 11 ነጥቦች ይዘውና በሶስተኛና በአራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠው የ9ኛ ሳምንት መርሃ ግብራቸውን በጅማ ከተማ ያካሔዱት የሁለቱም ክለቦች ጨዋታ በባለሜዳው ጅማ አባጅፋር 3ለ0 አሸናፊነት ተጠናቋል ።

አሸናፊው ጅማ አባጅፋር በተመስገን ገብረኪዳን፣ በዮናስ ገረመውና በንጋቱ ገብረስላሴ አማካኝነት ሶስት ግቦችን አስቆጥሯል ።

በ45ኛው ደቂቃ ሁለተኛውን ግብ ያስቆጠረው ዮናስ ገረመው ከግቧ መቆጠር በኋላ በጉዳት ከሜዳ የወጣ ሲሆን በ6 ግቦች ሊጉን በኮኮብ ግብ አስቆጣሪነት የሚመራው ኦኪኪ አፍላቢም ጉዳት አጋጥሞታል።

ጅማ አባጅፋር ማሸነፉን ተከትሎ ደረጃውን ከ3ኛ ወደ 2ኛ ከፍ ሲያደርግ ተሸናፊው ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ደግሞ ከ4ኛ ወደ 8ኛ ደረጃ ዝቅ ብሏል፡፡

 

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ