አርዕስተ ዜና

ድሬዳዋና ፋሲል ከነማ አንድ እኩል ተለያዩ

31 Dec 2017
477 times

ድሬዳዋ ታህሳስ 21/2010 ዛሬ በድሬዳዋ ከተማ በተካሔደው የዘጠነኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የወንዶች እግር ኳስ ውድድር ባለሜዳው ድሬዳዋ ከነማ ከፋሲል አቻው ጋር አንድ እኩል ተለያይቷል።

ዋና አሰልጣኙን አቶ ዘላለም ሽፈራውን ያሰናበነተው ክለቡ በምትኩ እየተመራ ባደረገው ግጥሚያ ነጥብ ተጋርቶ ለመውጣት ችሏል።

የክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ እስከዳር ዳምጠው ቀደም ሲል በላኩት መግለጫ እንዳመለከቱት ክለቡ አምና ከመውረድ ለጥቂት መትረፉን በማስተዋል በበርካታ ሚሊዮን ብር አዳዲስና ጠንካራ ተጨዋቾችን ቢያስፈርምም እስከ አሁን የተመዘገበው ውጤት አርኪ አይደለም።

ይህን ተከትሎም ዋና አሰልጣኙ ያስገቡት የመልቀቂያ ደብዳቤ ተቀባይነት በማግኘቱም እንዲሰናበቱ መደረጉን አመልክተዋል።

የክለቡ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ፍፁም ክንድሽ ለኢዜአ ዛሬ እንደገለፁት   የክለቡ አመራሮች፣ የክለቡ ቦርድና ተጫዋቾች  ክለቡ ባለፉት ጨዋታዎች ያስመዘገበውን ደካማ ውጤት ለመካስ የሚያስችል የጋራ መግባባት ፈጥረዋል።

ተጫዋቾቹም በቁጭት ተነቃቅተው ለቀጣይ ውድድሮች መዘጋጀታቸውን ጠቁመው የክለቡ ደጋፊዎችና የስፖርት ቤተሰቡ እንደሁልጊዜው በስታዲየም በመገኘት ድጋፋቸውን እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል።

ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር አንድ ተስተካካይ ጨዋታ የሚቀረው ድሬዳዋ ከነማ እስከ አሁን ካደረጋቸው ጨዋታዎች ሁለት ተሸንፎ ፤ አምስት አቻ ወጥቶ አንድ ጨዋታ በማሸነፍ ስምንት ነጥብ ይዟል።

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ