አርዕስተ ዜና

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአምስት ከተሞች የሩጫ ውድድር ሊያካሂድ ነው

05 Dec 2017
1028 times

አዲስ አበባህዳር 26 /2010 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 75ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ምክንያት በማድረግ በአምስት ከተሞች የሩጫ ውድድር ሊያካሂድ ነው።

ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የሚዘጋጀው የሩጫ ውድድር ታህሳሰ 8 ቀን 2010 ዓ.ም በሀዋሳ ከተማ በ7 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር ውድድር የሚጀመር ይሆናል።

በቀጣይም በተመሳሳይ ርቀት በሌሎች ከተሞች የሚቀጥል ሲሆን መቀሌ ላይ ታህሳስ 15 ቀን 2010 ዓ.ም ይካሄዳል።

ጥር 6 ባህርዳር ላይ የካቲት 18 ቀን 2010 ዓ.ም ደግሞ በአዳማ እንደሚካሄድ ታውቋል።

በክልል ከተሞች በሚካሄዱት ሁሉም ውድድሮች 3 ሺህ ያህል ተወዳዳሪዎች የሚካፈሉ ሲሆን አሸናፊዎች ከ10 ሺህ እስከ ስድስት መቶ ብር ሽልማት ያገኛሉ።

የውድድሩ ማጠቃለያ በአዲስ አበባ የሚደረግ ሲሆን በዚህ ውድድር 7 ሺህ 500 ተወዳዳሪዎች እንደሚሳተፉና አሸናፊውም የ75 ሺህ ብር ሽልማት እንደሚያገኝ ባንኩና ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በጋራ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

በዚህ የሩጫ ውድድር ከአትሌቶች በተጨማሪ የባንኩ ስራ አስኪያጆችና ሰራተኞች የሚካፈሉ ይሆናል።

 

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ