አርዕስተ ዜና

የ13ኛው ዙር የፕላን ኢንተርናሽናል የህጻናት ሩጫ ውድድር ምዝገባ ሰኞ ይጀመራል

12 Oct 2017
1730 times

አዲስ አበባ ጥቅምት 2/2010 13ኛው ዙር የፕላን ኢንተርናሽናል የህጻናት የሩጫ ውድድር ምዝገባ በመጪው ሰኞ እንደሚጀመር ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አስታወቀ።

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በዚህ ዓመት የሚያካሂዳቸውን የህጻናት የሩጫ ውድድር፣ 17ኛውን ቶታል ታላቁ ሩጫና ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅቱን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።

ህዳር 16 ቀን 2010 ዓ.ም የሚካሄደው የህጻናት ሩጫ ውድድር ምዝገባ በታላቁ ሩጫ ቢሮና በሂልተን ሆቴል እንደሚካሄድ ተገልጿል።

ውድድሩ በሶስት የዕድሜ ክልሎች ማለትም ከ5፣ ከ8 እና ከ11 ዓመት በታች ባሉ ሴትና ወንድ ህጻናት መካከል የሚደረግ ይሆናል።

የህጻናት ሩጫ ውድድሩ መነሻና መድረሻውን የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚን በማድረግ የሚከናወን ሲሆን 3 ሺህ 500 ህፃናት እንደሚሳተፉበት ይጠበቃል።

የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኤርሚያስ አየለ ለውድድሮቹ ከዚህ ቀደሙ የተለየ ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል።

44 ሺህ ሰዎች ይሳተፋበታል ተብሎ በሚጠበቀውና ህዳር 17 ቀን በሚካሄደው የ10 ኪሎ ሜትር ሩጫ የውጭና የአገር ውስጥ ሙዚቀኞች የሚሳተፉበት የሙዚቃ ኮንሰርት መኖሩን ጠቁመዋል።

በአፍሪካ ልዩ ድምቀት እየፈጠረ በመጣው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በዚህ ዓመትም በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ ሴቶች፣ ህጻናትና በዕድሜ የገፉ አዛውንቶችን ለመደገፍ የሚውል 1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር ለመሰብስብ መታቀዱ ተነግረዋል።

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ባለፉት አምስት ዓመታት "ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለሁ" በሚል የገቢ ማሳባሰቢያ ዘመቻ ያገኘውን 9 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር ለህጻናት፣ ሴቶችና አረጋዊያን ድጋፋ ለሚያደርጉ ድርጅቶች መስጠቱ ተገልጿል።

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ