አርዕስተ ዜና

የአዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ዋንጫ ዛሬ በሁለት ጨዋታዎች ይጀመራል

08 Oct 2017
1804 times

አዲስ አበባ መስከረም 28/2010 12ኛው የአዲስ አበባ ከተማ የእግር ኳስ ዋንጫ ውድድር ዛሬ በሚካሄዱ ሁለት ጨዋታዎች ይጀመራል።

በመክፈቻው ጨዋታ በምድብ 'ሀ' የተደለደለው ኢትዮጵያ ቡና ከቀኑ 10 ሠዓት ላይ ከጅማ አባ ጅፋር ይጋጠማል።

ከዚህ ጨዋታ ቀደም ብሎም በ8 ሠዓት ደደቢት ከአዲስ አበባ ከተማ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

ጨዋታው ከነገ በስቲያ ቀጥሎ የሚካሄድ ሲሆን በምድብ 'ለ' የተደለደሉት ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክና አዳማ ከተማ ከቀኑ በ9 ሠዓት፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከመከላከያ ደግሞ ከቀኑ 11 ሠዓት ከ30 ይጫወታሉ።

በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ጨዋታ የስታዲየም መግቢያ ዋጋ ይፋ የሆነ ሲሆን ክቡር ትሪቡን 150 ብር፣ ጥላ ፎቅ 100 ብር፣ ከማን አንሼ በወንበር 50 ብር ሆኗል።

ከማን አንሼ ያለ ወንበር እና ካታንጋ 20 ብር ሲሆን ሚስማር ተራና ዳፍ ትራክ 10 ብር የመግቢያ ዋጋቸው ነው።

በ1998 ዓ.ም በተጀመረው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ቀደም ሲል በነበሩ 11 የዋንጫ ጨዋታዎች ተጋባዥ የክልል ክለቦች ለዋንጫ ደርሰው ማሸነፍ ቢችሉም ዋንጫውን መውሰድ አይችሉም ነበር።

በዚህ ዓመት በአመራሮች በተደረገ ውይይት ተጋባዥ የሆኑት አዳማ ከተማና ጅማ አባ ጅፋር ካሸነፉ ዋንጫውን መውሰድ እንደሚችሉ ተወስኗል።

ዛሬ የሚጀመረውና በሁለት ምድቦች ተከፍሎ የሚካሄደው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ጨዋታ ጥቅምት 12 ቀን 2010 ዓ.ም ይጠናቀቃል።

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ