አርዕስተ ዜና
×

Warning

JUser: :_load: Unable to load user with ID: 452

የኢትዮጵያ ዳርት ፌዴሬሽን ከፍተኛ የበጀት እጥረት እንደገጠመው አስታወቀ

07 Oct 2017
1569 times

አዲስ አበባ መስከረም 27/2010 የኢትዮጵያ ዳርት ፌዴሬሽን በገጠመው የበጀት እጥረት ስፖርቱን ለማስፋፋት እንደተቸገረ ገለጸ።

ፌዴሬሽኑ ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤውን ዛሬ  በአዲስ አበባ አካሂዷል።

የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ ተስፋዬ ጎይቴ በወቅቱ እንደተናገሩት ፌዴሬሽኑ በገጠመው አጠቃላይ የበጀት እጥረት ስፖርቱን ለማስፋፋት አልቻለም።

የገንዘብ እጥረቱ የተፈጠረው ከወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር በየዓመቱ የሚመደበው ገንዘብ "ድጋፍ  በቂ ባለመሆኑና ስፖንሰር ማግኘት ባለመቻሉ ነው" ብለዋል። 

ፌዴሬሽኑ በዚህ ወር እየተካሄደ ባለው በጃፓኑ ዓለም አቀፍ የዳርት ሻምፒዮና በገንዘብ እጥርት መሳተፍ አልቻለም።

በመሆኑም ፌዴሬሽኑ "ከዓለም አቀፉ የዳርት ፌዴሬሽኖች ማህበር የሚያገኘውን ድጋፍ በቀላሉ ማግኘት ይከብደዋል" ብለዋል።

በኢትዮጵያ የሚገኙ የስፖርት ፌዴሬሽኖች በመንግስት ከሚደረግላቸው የገንዘብ ድጋፍ በተጨማሪ በስፖንሰር አቅማቸውን እንዲያሳድጉ የተፈቀደ መሆኑን ያስታወሱት አቶ ተስፋዬ የፌዴሬሽኑ ለተቋሞች የሚያቀርበው የስፖንሰር ሺፕ ጥያቄዎች ምላሽ እንደማያገኙ ገልፀዋል።

ተሳታፊዎች በበኩላቸው ፌዴሬሽኑ ከመንግስት ድጎማ መላቀቅና ያለበትን የገንዘብ ችግር ለመፍታት ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባው አሳስበዋል።

ለክልሎች የሚደረገው ክትትልና ድጋፍ  በቂ አለመሆኑን የተናገሩት ተወያዮቹ፤ ያለው የቁሳቁስ እጥረትና የታዳጊ ፕሮጀክቶች አለመስፋፋት ለስፖርቱ እድገት ማነቆዎች መሆናቸውን ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ዳርት ፌዴሬሽን በየዓመቱ ከወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር 285 ሺህ ብር ዓመታዊ ድጎማ ይደረግለታል።

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ