አርዕስተ ዜና
×

Warning

JUser: :_load: Unable to load user with ID: 452

ቅዱስ ጊዮርጊስ አዲስ አሰልጣኝ ሾመ

13 Sep 2017
1284 times

አዲስ አበባ መስከረም 3/2010 የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ ፖርቱጋላዊው ካርሎስ ማኑዌል ቫዝ ፒንቶ አዲሱ የክለቡ ዋና አሰልጣኘ አድርጎ ሾመ።

ክለቡ ፈረሰኞቹን ላለፉት ሁለት ዓመታት በዋና አሰልጣኝነት የመሩት ሆላንዳዊው አሰልጣኝ ማርት ኖይ በጤና እክል ምክንያት ከክለቡ መለያየታቸውን ተከትሎ ነው አዲስ አሰልጣኝ የሾመው።

ክለቡ በድረ ገጹ እንዳስነበበው የ43 ዓመቱ ፖርቱጋላዊው አሰልጣኝ ካርሎስ ማኑዌል ቫዝ ፒንቶ ለቀጣይ ሁለት ዓመታት ከፈረሰኞቹ ጋር እንደሚቆይ አስታውቋል።

አዲሱ አሰልጣኝ የካፍና የዩኤፍ የአሰልጣኝነት ኤ ላይሰንስ ያላቸው ሲሆኑ፤ ቅዱስ ጊዮርጊስን ከመረከባቸው በፊት የአንጎላውን ሪክሬቲቮ ክለብ በማሰልጠን ላይ ነበሩ።

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ