አርዕስተ ዜና

ፌዴሬሽኑ ጉባኤውን ያካሄደው ደንቡን መሰረት በማድረግ መሆኑን ገለጸ

08 Sep 2017
1239 times

አዲስ አበባ ጳጉሜ 3/2009 ''የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ነሐሴ 20 ቀን 2009 ዓ.ም ያካሄድኩት ጠቅላላ ጉባኤ ህጋዊ አልነበረም መባሉ አግባብ አይደለም '' አለ።

ፌዴሬሽኑ በወቅቱ  ባካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ደንብ ጥሰዋል ባላቸው አራት የስራ አስፈጻሚ አባላት ላይ እገዳ መጣሉ  ቅሬታ አስነስቷል።

የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈጻሚ ህጋዊ በሆነው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ካለበቂ ምክንያት አልተገኙም ባላቸው የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳነት በነበሩት አቶ አማረ ማሞ፣ተቀዳሚ ፕሬዚዳነት በነበሩት አቶ ጌታቸው ገብረማሪያምና በምክትል ፕሬዚዳንትነት ሲሰሩ በነበሩት አቶ ኃይሉ ሞላ ላይ እገዳ መጣሉ ይታወሳል።

ይህንን ተከትሎ የፌዴሬሽኑ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ጌታቸው ገብረማሪያም አውቅና የሌለውና ህገ ወጥ ጠቅላላ ጉባኤ ተደርጓል በማለት ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ቅሬታቸውን በደብዳቤ ማሰማታቸውና ለተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን መናገራቸውም ነው የተገለጸው።

የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ጊዜያዊ ሰብሳቢ አቶ በለጠ ዘውዴ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ያሰታወቁት የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈጻሚ አባላት የ2009 ዓ.ም  ጠቅላላ ጉባኤው ነሐሴ 20 እንዲካሄድ በአብላጫ ድምጽ ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት ነው ጠቅላላ ጉባኤው የተከናወነው።

ይህም የኢትዮጵያ፣ የዓለም አቀፉንና የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን  ህግና ደንብ መሰረት ባደረገ መልኩ ጠቅላላ ጉባኤው መካሄዱንና  ውሳኔ መተላለፉን ነው አቶ በለጠ የተናገሩት። 

ይሁን እንጂ አቶ ጌታቸው ገብረማሪያም ጠቅላላ ጉባኤው የሚካሄድበትን ቀን እያወቁ በወቅቱ በጠቅላላ ጉባኤው ላይ ባለመገኘታቸው በደንቡ መሰረት በፌዴሬሽኑ ስራ አስፈጻሚ አባላት ድምጽ እንዲታገዱ ተወስኗል ብለዋል።

በመሆኑም ስራ አስፈጻሚው ያጸደቀውን ውሳኔ ህግ ወጥ ነበር ማለት አግባብነት እንደሌለው ገልጸዋል። 

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ