አርዕስተ ዜና

የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ መስከረም 20 ይጀመራል

08 Sep 2017
1409 times

ጳጉሜን 3/2009 የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት ለ12ኛ ጊዜ የሚካሄደው የመዲናዋ እግር ኳስ ዋንጫ ውድድር መስከረም 20 ቀን 2010 ዓ.ም ለመጀመመር ታቅዷል።

የከተማዋ ኳስ ፌዴሬሽን ዛሬ በሰጠው መግለጫ ውድድሩ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ የሆኑ አምስት የአዲስ አበባና ሦስት ተጋባዥ ክለቦችን በማሳተፍ በአዲስ አበባ ስታዲየም የፊታችን መስከረም 20 ይጀመራል ።

የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ጊዜያዊ ሰብሳቢ አቶ በለጠ ዘውዴ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት ውድድሩ ከመስከረም 20 እስከ ጥቅምት 4 ቀን 2010 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም ይቆያል።

በውድድሩ በድምሩ ስምንት ክለቦች እንደሚካፈሉ አቶ በለጠ ገልጸው ተሳታፊ ክለቦች በቀጣይ ስማቸው ይፋ እንደሚሆንም ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ክለብ የሆኑት ኢትዮጵያ ቡና እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ የደቡብ ክልል ክለቦችን በሚያሳትፈው ''በሴንትራል ሀዋሳ ሲቲ ካፕ'' ውድድር እንደሚካፈሉም ይነገራል።

''እነዚህ ክለቦች በአዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ዋንጫ ለመሳተፍ የመርሃ ግበር መጣረስ አያጋጥማቸውም ወይ የሚል ጥያቄ ከጋዜጠኞች ተነስቷል።

የሀዋሳው ሲቲ ካፕ ውድድር ከመስከረም 6 እስከ 14 ቀን 2010 ዓ.ም የሚካሄድ በመሆኑ ፕሮግራም አይጣረስም፤ ክለቦችም በሁለቱ የውድድር አይነቶች እንደሚካፈሉ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አቶ በለጠ ጠቅሰዋል ።

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሚሳተፉ ክለቦች ቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን የሚለኩበት መሆኑን የገለጹት አቶ በለጠ በውድድሩ የሚገኘው ገንዘብ ፌዴሬሽኑ ለሚያዘጋጃቸው የውስጥ ውድድሮች የሚውል መሆኑን ጠቅሰዋል።

 

 

 

 

 

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ