አርዕስተ ዜና

የጅማ ከተማ እግር ኳስ ክለብ መጠሪያውን ወደ ጅማ አባ ጅፋር ሊቀይር ነው

07 Sep 2017
857 times

ጅማ  ጳጉሜ 2/2009  ወደ  ኢትየጵያ ፕሪሚየር ሊግ የተቀላቀለው   የጅማ ከተማ የእግር ኳስ ክለብ በአዲሱ የውድድር ዓመት " ጅማ አባ ጅፋር" በሚል ስያሜ እንደሚጠራ የክለቡ ፕሬዚዳንት ገለፁ ።

ፕሬዚዳንቱ አቶ ሁሴን ዝናብ እንደገለፁት ክለቡ የከተማውን  ታሪክ፣ ወግ፣ ልማድና ባህል የሚወክል መጠሪያ እንዲኖረው በማሰብ ጅማ  አባጅፍር እግር ኳስ ክለብ በሚል ስያሜ እንዲጠራ ለከተማው ምክር ቤት አቅርቦ ለማፀደቅ ዝግጅት ተደርጓል ።

" የክለቡ ስም ወደ ጅማ አባጅፋር መለውጡ ክለቡን የበለጠ ህዝባዊ ውክልና እንዲኖረውና  መሰረቱ እንዲሰፋ ያግዘዋል "ብለዋል ።

የከተማ አስተዳደር የስራ ኃላፊዎች ክለቡን በገቢ ለማጠናከር የአንድ ወር ደመወዛቸው የለገሱ መሆናቸውንም  የክለቡ ፕሬዚዳንት ጠቁመዋል።

ጅማ ከተማ እግር ኳስ  ክለብ በ1970 ዓ.ም  መመስረቱን ከክልቡ የተገኘው መረጃ ይጠቁማል፡፡

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ

<!-Foreign Exchange Rates widget - HTML code - fx-rate.net -->

<!-end of code-->

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ