አርዕስተ ዜና
×

Warning

JUser: :_load: Unable to load user with ID: 452

3ኛው የኮካ ኮላ ሀገር አቀፍ የወጣቶች እግር ኳስ ውድድር ተጠናቀቀ

04 Sep 2017
1459 times

ጅግጅጋ  ነሀሴ 29/2009 በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንና ኮካ ኮላ ኩባንያ ትብብር ከነሀሴ 20 ቀን 2009 ዓ.ም ጀምሮ ለዘጠኝ ቀናት ሲካሄድ የቆየው ከ15 ዓመት በታች የወጣቶች የኮፓ ኮካ ኮላ እግር ኳስ ውድድር ትናንት ፍጻሜውን አገኘ።

በጅግጅጋ ከተማ ከሁሉም ክልሎች እና ሁለት የከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ ከ500 በላይ ስፖርተኞች የተሳተፉበት ዓመታዊ የኮፓ ኮካ ኮላ እግር ኳስ ውድድር በወንዶች በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል፤ በሴቶች ደግሞ በደቡብ ክልል አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

በወንዶች የፍጻሜ ውድድር የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ቡድን የአማራ ክልልን 4 ለ1 ሲያሸንፍ፤ በሴቶች ደግሞ ደቡብ ክልል አማራን 5 ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

ብዙ ጎል በማስገባት በወንዶች የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ተጫዋች አብዱላሂ አብዲአዚዝ 6 ግቦችን በማስቆጠር እንዲሁም በሴቶች የደቡብ ክልል ተጫዋች አምሳል ፍሰሃ 12 ግብ በማስቆጠር ተሸላሚ ሆነዋል፡፡

በውድድሩ በወንዶች የጋምቤላ ክልል፤ በሴቶች ደግሞ የሐረሪ ክልል ቡድኖች የጸባይ ዋንጫ ሽልማት አግኝተዋል፡፡

በውድድር መስፈርቱ መሰረት በትክክለኛ የዕድሜ ክልል ላይ ያሉ ተጫዋቾችን በማቅረብ በኩል በወንዶች ሐረሪ፤ በሴቶች ደግሞ አዲስ አበባ ተጠቃሽ ናቸው።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ አብዲወሊ መሀመድና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም መሀድ በውድድሩ ፍጻሜ ላይ ተገኝተው አሸናፊ ለሆኑ ክልሎች የተዘጋጀውን የዋንጫ ሽልማት አበርክተዋል፡፡

ከነሀሴ 20 እስከ 28 ቀን 2009 ዓ.ም በተካሄደው በእዚህ ውድድር 30 ሴቶች እና 30 ወንዶች ወደ ስፖርት ማዕከላት ገብተው እንዲሰለጡኑ መመረጣቸውን በሽልማት ሥነ-ስርአቱ ላይ ይፋ ተደርጓል፡፡

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ