አርዕስተ ዜና

አትሌት ሙክታር እድሪስ በ5000ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ አስገኘ Featured

13 Aug 2017
1389 times

ነሐሴ 6/ 2009 በለንደን  በተካሄደው 16ኛው የዓለም አትሌቲክሰ ሻምፒዮና በወንዶች የ5 ሺህ ሜትር የፍጻሜ ውድድር አትሌት ሙክታር እድሪስ  የወርቅ ሜዳሊያ አስገኘ፡፡

አትሌት ሙክታር ውድድሩን በ13 ደቂቃ 32 ሴከንድ 79 ማይክሮ ሰከንድ  በመግባት  ውድድሩን በአንደኝነት አጠናቋል፡፡

በውድድሩ ኢንግሊዛዊው ሞ ፋራህ 13 ደቂቃ 33 ሰከንድ 22 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት  ሁለተኛ ሲወጣ፣ ዮሚፍ ቀጄልቻ አራተኛና ሰለሞን ባረጋ አምስተኛ ወጥቷል።

እስካሁን በተካሄደው 16ኛው የዓለም  ሻምፒዮና  ኢትዮጵያ ሁለት የወርቅ እና ሁለት የብር ሜዳሊያዎችን  አግኝታለች፡፡

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ