አርዕስተ ዜና
×

Warning

JUser: :_load: Unable to load user with ID: 452

የወንዶች 5 ሺህ ሜትር የፍጻሜ ውድድር ዛሬ ምሽት ይደረጋል

12 Aug 2017
1018 times

አዲስ አበባ ነሀሴ 6/2009 በለንደኑ የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የወንዶች 5 ሺህ  ሜትር የፍጻሜ ውድድር ዛሬ ምሽት ይደረጋል።

ዛሬ ምሽት 4 ሰዓት ከ20 ላይ በሚካሄደው የወንዶች 5 ሺህ ሜትር የፍጻሜ ውድድር ኢትዮጵያ በርቀቱ በአትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ፣ ሰለሞን ባረጋና ሙክታር እንድሪስ ትወከላለች፡፡

በአትሌቲክስ ስፖርት አፍቃሪያን ዘንድ አድናቆት የተቸረው እንግሊዛዊው ሞህ ፋራህ  በፍጻሜው ውድድር ይሳተፋል።

አትሌቱ በሻምፒዮናው በ 10 ሺ ሜትር ውድድር ወርቅ ማጥለቁ ይታወሳል፡፡

በምሽቱ የፍጻሜ ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች፣ ከሞህ ፋራህና በሪዮ ኦሎምፒክ የ5 ሺህ ሜትር የብር ሜዳሊያ ባለቤት ከሆነው አሜሪካዊው ፓዩል ችሊሞ ከፍተኛ ትንቅንቅ ይጠብቃቸዋል፡፡

ትናንት ምሽት በተከናወነው የሴቶች 3 ሺህ መሰናክል ኢትዮጵያ ድል ሳይቀናት ቀርቷል።

በ3 ሺህ መሰናክል ከተወዳደሩት ሁለት ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች መካከል አትሌት እቴነሽ ዲሮ ሰባተኛ ሆና ስታጠናቅቅ  አትሌት ብርቱካን ፈንቴ ደግሞ ውድድሩን አቋርጣለች።

በርቀቱ አሜሪካ የወርቅና የብር ሜዳሊያውን ስትወስድ ኬኒያ የነሀስ ሜዳሊያ ማግኘት ችላለች።

በዚህ ርቀት የአሸናፊነት ግምት የተሰጣት ኬኒያዊቷ አትሌት ቢትሪይስ ኪፕኮች አንደኛው መሰናከል ላይ ስትደርስ መሰናክሉን ሳትዘል በመሙ በመሯጧ  ወደ ኋላ ለመቅረት ተገዳለች።

የተወሰነ ሜትር ከሮጠች በኋላ እንደገና ወደ ኋላ በመመለስ መሰናክሉን በመዝልለ ውድድሯን ብትቀጥልም ሜዳሊያ ማጥለቅ አልቻለችም ፤ ቢትሪይስ ኪፕኮች ውድድሩን አራተኛ ሆና አጠናቃለች፡፡።

ነገ ፍጻውን የሚያገኘው 16ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና እስካሁን በተደረጉት ውድድሮች አሜሪካ በስምንት ወርቅ፣ ስምንት ብርና ሰባት ነሐስ በድምሩ በ23 ሜዳሊያ በአንደኝነት እየመራች ነው።

ኬኒያ በሶስት ወርቅ፣ አንድ ብርና አራት ነሀስ በድምሩ ስምንት ሜዳሊያ በማግኘት በሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

ኢትዮጵያ  አንድ ወርቅና ሁለት ብር በማግኘት በደረጃ ሰንጠረዥ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ