አርዕስተ ዜና
×

Warning

JUser: :_load: Unable to load user with ID: 452

ኢትዮጵያ በፊፋ ወርሃዊ የደረጃ ሰንጠረዥ 16 ደረጃዎችን አሻሻለች

10 Aug 2017
1054 times

አዲስ አበባ ነሀሴ 4/2009 አለም አቀፉ እግር ኳስ ማህበር /ፊፋ /በሚያወጣው ወርሃዊ ሪፖርት ኢትዮጵያ 16 ደረጃዎችን አሻሻለች።

የኢትዮጵያ ወንዶች ብሄራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) በሰኔ ከነበረበት 136ኛ አስራ ስድስት ደረጃዎችን በማሻሻል 120ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ዋልያዎቹ በቻን ማጣሪያ የጅቡቲ አቻቸውን 5 ለ1 አሸንፈው ከዛምቢያ ብሄራዊ ቡድን ጋር  በአቋም መፈተሻ ጨዋታ ያለ ግብ  መለያየታቸው ለደረጃ ሰንጠረዥ መሻሻል አስተዋጽኦ አድርጓል።

ኢትዮጵያ በዓለም እግር ኳስ 120ኛ ደረጃ ላይ ስትቀመጥ  ከአፍሪካ አገሮች 36ኛ ደረጃን ይዛለች።

ግብጽ ከዓለም 25ኛ ደረጃ ላይ ስትቀመጥ የአፍሪካን  ደረጃ በአንደኝነት እየመራች ነው።

ዲሞክራቲክ ኮንጎና ሴኔጋል ከዓለም 28ኛ እና 31ኛ ደረጃ ላይ የያዙ ሲሆን ፤ በአፍሪካ  ደግሞ ሁለተኛና ሶሰተኛ ደረጃን ለመያዝ ችለዋል።

ብራዚል የዓለም አቀፍ እግር ኳስ ደረጃን በቀዳሚነት ስትመራ ጀርመን፣ አርጀንቲና ፣ ስዊዘርላድና ፖላንድ ከሁለት እስከ አምስት ያለውን ደረጃ  መያዝ ችለዋል።

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ