አርዕስተ ዜና
×

Warning

JUser: :_load: Unable to load user with ID: 452

በዓለም ከ18 ዓመት በታች ሻምፒዮና የተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑክ አዲስ አበባ ገባ Featured

17 Jul 2017
2007 times

አዲስ አበባ ሐምሌ 10/2009 በኬንያ በተደረገው 10ኛው የዓለም ከ18 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን ወክለው የተወዳደሩ አትሌቶች አዲስ አበባ ገቡ።

በሻምፒዮናው ታሪካዊ ውጤት ያስመዘገቡ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን አባላት ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ አቀባበል ተደረጎላቸዋል።

በአቀባበል ሥነ ሥርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴና የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስን ጨምሮ ሌሎች አካላት ተገኝተዋል።

 አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ በኬንያ በተካሄደው የዓለም ከ18 አመት በታች ሻምፒዮና ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ያሳዩት የቡድን ስራ  የሚያኮራ ነው ብሏል።

የቡድን ስራ በመሰራቱ ታሪካዊ ውጤት ሊመዘገብ መቻሉን ገልጾ ይህም በሌሎች አትሌቶች መደገም እንዳለበት አሳስቧል።

ኬንያ ውድድሩን በተሳካ ሁኔታ ማስተናገድ መቻሏ የሚደነቅ ነው ያለው አትሌት ኃይሌ “እኛም በአመራር ዘመናችን ይህን መሰል ዓለም አቀፍ ውድድሮች ለማስተናገድ ዕቅድ አለን” ብሏል።

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ እንደተናገሩት በወጣቶች የተመዘገበው ውጤት ተቀዛቅዞ በነበረው የአትሌቲክስ ውጤት የተከፋውን ህዝብ የሚክስ ነው።

ውጤቱ ቀጣይነት እንዲኖረውም ኮሚቴው አስፈላጊውን ድጋፍ አንደሚያደርግ ቃል ገብተዋል።

የልዑክ ቡድኑ መሪ አቶ ዱቤ ጅሎ በበኩላቸው ለውድድሩ ትኩረት ሰጥተን ጠንካራ ልምምድ በማድረጋችን መልካም ውጤት አስመዝግበናል ብለዋል።

በ10ኛው የዓለም ከ18 ዓመት በታች ሻምፒዮና የዕድሜ ማጭበርበር ችግር መታየቱንም ገልጸዋል። 

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን የአትሌቶችን ዕድሜ ለማረጋገጥ በዋናነት የልደት ሰርተፍኬት፣ ቤተሰብና የትምህረት ቤት ማስረጃን ተጠቅሟል።

ነገር ግን አትሌቶች ሙሉ በሙሉ  ከ18 ዓመት በታች ናቸው ለማለት አስቸጋሪ መሆኑን ነው አቶ ዱቤ የተናገሩት።

የዕድሜ ተገቢነት ችግር ግን የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የሁሉም የአፍሪካ አገራት ችግር ነው ብለዋል።