አርዕስተ ዜና

የጅማ ዞን ዓመታዊ የክለቦች እግር ኳስ ውድድር ተጀመረ

17 May 2017
734 times

ጅማ ግንቦት 9/2009 በጅማ ዞን 30 ክለቦች  የሚሳተፉበት ዓመታዊ የገጠር ከተሞች የእግር ኳስ ውድድር ተጀመረ።

ውድድሩ ትናንት በጅማ ከተማ ሲጀመር የዞኑ  ስፖርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ካሳሁን ጆብር እንደገለጽት ዓላማው የዞኑን እግር ኳስ  ለማጠናከር ነው ።

በውድድር ላይ 30 ክለቦችና 608 ስፖርተኞች የሚሳተፉ  ሲሆን የዘንድሮው  ከአምናው ጋር ሲነፃፀር በስድስት ክለቦች ጭማሪ ማሳየቱን ጠቅሰዋል።

ለቀጣዮቹ 13 ቀናት በሚቆየው ውድድር አሸናፊ የሚሆነው ክለብ በኦሮሚያ የሊግ ሻምፕዮና ላይ ተሳታፊ እንደሚሆንም ተመልክቷል፡፡

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ