አርዕስተ ዜና

የጤና ባለሙያዎች የሚሳተፉበት የሩጫ ውድድር ሊካሄድ ነው

21 Apr 2017
458 times

አዲስ አበባ ሚያዝያ 13/2009 የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች የሚሳተፉበት የአምስት ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አስታወቀ።

ውድድሩ ሚያዚያ 22 ቀን 2009 ዓም የሚካሄድ ሲሆን መነሻውንና መድረሻውን ሰሚት አድርጓል።

የጤና ባለሙያዎች ማኅበር ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለሁለተኛ ጊዜ በሚያካሄደው ውድድር ከአምስት ሺህ በላይ የጤና ባለሙያዎችና የኅብረተሰብ ክፍሎች ተሳታፊ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ሥራ አስኪያጅ አቶ ኤርምያስ አየለ ለኢዜአ እንደተናገሩት ውድድሩ የጤና ባለሙያዎች ማኅበር ዓመታዊ በዓልን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ ነው።

በውድድሩ የጤና ባለሙያዎች በስፖርቱ ያላቸውን ተሳትፎ ለማጎልበት ጠቀሜታው የጎላ ነው ብለዋል።

አሸናፊ ለሚሆኑ ተወዳዳሪዎችም የገንዘብ ሽልማት መዘጋጀቱን የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አስታውቋል።

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ