አርዕስተ ዜና

የህጻናት ሩጫ ውድድር ሊካሄድ ነው

21 Apr 2017
480 times

አዲስ አበባ ሚያዝያ 13/2009 የህጻናት የሩጫ ውድድር በታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያና በአውሮፓ ህብረት አጋርነት በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው።

የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ስራ አስኪያጅ አቶ ኤርምያስ አየለ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ውድድሩ በየዓመቱ የሚከበረውን የአውሮፓ ቀን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ ነው።

ውድድሩ በሴቶችም በወንዶችም የሚደረግ ሲሆን ከ14 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ብቻ የሚሳተፉበት መሆኑን ነው የገለጹት።

እንደ አቶ ኤርምያስ ገለጻ በዚህ ውድድር ሶስት ሺህ የሚጠጉ ታዳጊዎች የሚሳተፉ ሲሆን የተለያዩ የትምህርት መሳሪያዎች በሽልማት መልክ ይበረከትላቸዋል ብለዋል።

ውድድሩ የሚካሄደው ቦሌ ክፍለከተማ በሚገኘው በኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ መሆኑንም ተናግረዋል።

ውድድሩ ሚያዚያ 28 ቀን 2009 ዓ.ም ይካሄዳል።

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ