አርዕስተ ዜና

የግማሽ ማራቶንና የሰባት ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር በአዋሳ ከተማ ይካሄዳል - ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ

21 Apr 2017
504 times

አዲስ አበባ ሚያዝያ 13/2009 የግማሽ ማራቶንና የሰባት ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር በመጪው እሁድ በአዋሳ ከተማ ይካሄዳል።

ውድድሩ በአዋሳ ከተማ ሲካሄድ ለስድስተኛ ጊዜ መሆኑን ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አስታውቋል።

የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ሥራ አስኪያጅ አቶ ኤርሚያስ አየለ ለኢዜአ  እንደተናገሩት፤  በውድድሩ ተሳታፊ በመሆንና ውጤት በማስመዝገብ በዓለም ዓቀፍ መድረኮች ላይ አገራቸውን ወክለው የሚወዳደሩ አትሌቶችን ለመለየት ያስችላል። 

ውድድሩ በሁለት መርሃ ግብሮች ተከፍሎ የሚካሄድ ሲሆን፤ የግማሽ ማራቶኑ ውድድር ለአትሌቶችና ለጤና ሯጮች የተዘጋጀ ነው።

የሰባት ኪሎ ሜትር ሩጫ ደግሞ "በሩጫው መሳተፍ የሚፈልጉ የህብረተሰብ ክፍሎችን ያማከለ ይሆናል" ብለዋል።

እንደ አቶ ኤርሚያስ ገለጻ፤ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በመቀናጀትና በመተባበር ውድድሩን በማሳደግና በማስፋፋት ቀጣይነት እንዲኖረው ያደርጋል። በተጨማሪም ህብረተሰቡ በስፖርቱ ተሳታፊ የሚሆንበትን መንገድ ለማመቻቸት ይጠራል።

ሚያዚያ 15 ቀን 2009 ዓ.ም. በሚካሄደው ውድድር ከሁለት መቶ በላይ የሚሆኑ ዜጎች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ከዚህ ውስጥ ከ30 እስከ 40 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች እነደሚሆኑ ታሳቢ ተደርጓል።

በግማሽ ማራቶን አሸናፊ ለሚሆኑ ተወዳዳሪዎች 20 ሺ ብር፤ ከዚያ በታች ለሚወጡ ደግሞ በየደረጃው የአስር ሺ ብር ሽልማት መዘጋጀቱ ተገልጿል።

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ