አርዕስተ ዜና
×

Warning

JUser: :_load: Unable to load user with ID: 452

በፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ድሬዳዋ ከነማን አሸነፈ

21 Apr 2017
527 times

ድሬዳዋ ሚያዝያ 13/2009 በ24ኛው ሣምንት የፕሪሚየር ሊግ የእግር  ኳስ ጨዋታ ትናንት ቅዱስ ጊዮርጊስ ድሬዳዋ ከነማን አምስት ለሶስት በሆነ ውጤት በማሸነፍ መሪነቱን አጠናክረ፡፡

ጊዮርጊስ ከረፍት በፊት የጨዋታ ጊዜ በ17ኛ ደቂቃ በመሐሪ መና ፣ በ33ኛ ደቂቃ በአዳነ ግርማና ፣ በ45ኛው ደቂቃ በሳላዲን ሰኢድ ባስቆጠራቸው ሶስት ጎሎች እረፍት ወጥቷል ።

ቡድኑ ከእረፍት መልስ በ69ኛው ደቂቃ ላይ በሳላአዲ ሰኢድና በ82ተኛው ደቂቃ በፕሪንሰ ሰቪሪኒሆ አማካኝነት ባስቆጠራቸው ሁለት ግቦች ጨዋታውን በአሸናፊነት አጠናቋል ።

ቡድኑ እስከ 70ኛው ደቂቃ የጨዋታ ብልጫ ነበረው።

ባንፃሩም  የድሬዳዋ ከነማ እስከ 80 ደቂቃ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ያሳዩት ከብቃት በታች ያልተጠበቀ ጨዋታ ተመልካቹን ግራ ያጋባ እንደነበር ተስተውሏል።

ይሁንና ቡድኑ በሜዳው አምስት ጎል ካስተናገደ በኋላ ተጫዋቾቹ ያሳዩት የኳስ ጥበብ በተመልካቾች ዘንድ ቀደም ሲል የት ነበሩ የሚል ጥያቄ አስንስቷል፡፡

ይህንኑ ተከትሎ በ85ኛ ደቂቃ በረከት ኢሳቅ፣ በ87ኛና በ92ኛ ደቂቃዎች በይሁን እንደሻው ሶስት ጎል ቢያስቆጥርም ጨዋታውን በሽንፈት ለማጠናቀቅ ተገዷል ።

ከጨዋታው በኋላ የጊዮርጊስ ምክትል አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ለማሸነፍ ተዘጋጅተው መምጣታቸውንና ይህንም ማሳካት መቻላቸውን ተናግረዋል፡፡

እስከ 70ኛው ደቂቃ ቡድናቸው ባሳየው ብቃት ለአሸናፊነት መብቃታቸውን ጠቅሰው ጨዋታው መገባደጃ ተጫዋቾቻቸው የፈጠሩት መዘናጋት ጎል ሊቆጠርባቸው እንደቻለም ጠቅሰዋል፡፡

"ዛሬ ተጫዋቾቼ በሙሉ  ከሚጠበቀው በታች ነው የተጫወቱት፤ ብቃታቸው ወርዷል፤ ቀደም ሲል ባደረግናቸው ጨዋታዎች የነበረን ብቃት አጠገባችን አልነበረም፤ በተለይ የዋና በረኛችን ሳምሶን አለመኖር ዋጋ አስከፍሎናል" ያሉት ደግሞ የድሬዳዋ ከነማ አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው ናቸው፡፡

በቀጣይ ከደደቢት ጋር በሚኖራቸው ጨዋታ ቡድኑን ወደ አሸናፊነት በመመለስ ደጋፊውን ለመካስ  እንደሚዘጋጁ አሰልጣኝ ዘላለም ተናግረዋል።

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ