አርዕስተ ዜና

በባህርዳር ከተማ ህዝባዊ የሩጫ ውድድር ተካሄደ

19 Mar 2017
533 times

ባህርዳር መጋቢት 10/2009 በባህርዳር ከተማ  አስር ኪሎ ሜትር የሸፈነ ስድስተኛው  ህዝባዊ ሩጫ ውድድር ዛሬ ተካሄደ።

የወድድሩ የበላይ አዘጋጅ አትሌት መልካሙ ፈንቴ እንደገለጸው  በሩጫው  በሁለቱም ጾታ  ከወረዳ፣ ከዞንና ከፌደራል የመጡ ከ6ሺህ በላይ ተወዳዳሪዎች ተሳትፈዋል፡፡

ህዝባዊ ሩጫውን በቀጣይ ወደ ናይል ማራቶን በማሳደግ የመላ አፍሪካና የዓለም አትሌቶች እንዲሳተፉበት ለማድረግም ከባህርዳር ከተማና ከክልሉ ባለድርሻ አካላት ጋር እየተሰራ መሆኑን ተናግሯል።

በወንዶች አያሌው ዓለሙ ከመከላከያ አትሌቲክስ፣ ጌታቸው ማስረሻ ከደባርቅ፣ ታደሰ ተስፋሁን ከአማራ ማረሚያ አትሌትክስ ክለብ በቅደም ተከተል ከአንድ እስከ ሶስተኛ ወጥተዋል።

በሴቶችም አስናቀች አወቀ ከአማራ ማረሚያ፣ በላይነሽ አዲስ ከደጋ ዳሞትና አለምአዲስ እያዩ ከሰሜን ጎንደር አትሌቲክስ ክለቦች አሸናፊ ሆነዋል።

በሁለቱም ጾታ አንደኛ ለወጡት ለእያንዳንዳቸው የአስር ሺህ ብር፣ ሁለተኛ ለሆኑት ስድሰት ሺህ እና በሶስተኛነት ላጠናቀቁት ደግሞ አራት ሺህ ብር እያለ እስከ ስድስተኛ ድረስ  ለወጡት እንደየደረጃቸው የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ከባህርዳር ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ የውድድሩ የቴክኒክ አስተባባሪ አቶ አንዷለም አሊ በበኩላቸው ውድድሩ በየዞኑ ለተቋቋሙ የአትሌቲክስ ክለብ የአቋም መለኪያ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

" ክልሉን ወክለው በአገር አቀፍ በሂደትም በዓለም ደረጃ ሊወዳደሩ የሚችሉ ብቁ ተተኪ አትሌቶች እንደሚወጡ  በውድድሩ ማየት ተችሏል "ብሏል።

 

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ