አርዕስተ ዜና

የሜድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ዓመታዊ የስፖርት ውድድር ተጀመረ

05 Mar 2017
545 times

አዲስ አበባ የካቲት 26/2009 የሜድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎችና ተጋባዥ ተቋማት 14ኛው ዓመታዊ የስፖርት ውድድር ዛሬ በአዲስ አበባ ተጀመረ።

ለሶስት ወራት የሚቆየው የስፖርት ውድድር ሳር ቤት በሚገኘው መቻሬ ሜዳ የኩባንያው ሠራተኞችና ቤተሰቦቻቸው በተገኙበት ተጀምሯል።

በውድድሩ 25 የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎች ተካፋይ ይሆናሉ።

የሜድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር አረጋ ይርዳው ውድድሩ ሲጀመር እንደገለጹት፤ የውድድሩ ዓላማ የሠራተኞችን የእርስ በርስ ግንኙነት ለማጎልበት፣ ጤናማ የኩባንያ የሥራ መንፈስ ለማስፈን ነው።

የዚህ ዓይነቱ ውድድር አዳዲስ ተተኪ ስፖርተኞችን ለማበረታትና በኩባንያዎች መካከል ያለውን ወዳጅነት እንዲጠናከር ለማድረግ እንደሚያግዝ ተናግረዋል።

የውድድሩን ፍጻሜ በአዲሱ የወልድያ ስታዲየም ለማድረግ ዕቅድ መያዙንም ዶክተር አረጋ ጠቅሰዋል።

እግር ኳስ፣መረብ ኳስ፣ ሩጫ፣ ሜዳ ቴኒስና ሌሎች ስፖርቶች የውድድር ዓይነቶች ናቸው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ 25ቱ የሜድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎች ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚውል የሦስት ሚሊዮን ብር ቦንድ እንደሚገዙ ተናግረዋል።

እንደ ዶክተር አረጋ ገለጻ፤ ከኩባንያዎች በተጨማሪ ሠራተኞችም ቦንድ እንዲገዙ ይደረጋል።

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ