አርዕስተ ዜና

በሊጉ ጨዋታ ወላይታ ድቻ ወልዲያን 2 ለ0 አሸነፈ

581 times

ሶዶ መጋቢት 2/2010 ዛሬ በወላይታ ሶዶ ሁለገብ ስታዲየም  በተካሄደው ተስተካካይ ጫወታ የወንዶች ፕሪሚየር ሊግ እግር ኳስ ጨዋታ ወልዲያን ያስተናገደው ወላይታ ድቻ ሁለት ለባዶ በሆነ ውጤት አሸነፈ።

የወላይታ ድቻ እግር ኳስ ቡድን ጎሎችን ያስቆጠረው በሁለተኛው የጨዋታ ክፍሌ ጊዜ ሲሆን የመጀመሪያውን በ67ኛ ደቂቃ ላይ 14 ቁጥር ለብሶ የተጫወተው አምሬላ ደልታታ አስቆጥራል።

አሥር ቁጥሩ ጃኮ አራፋት ሁለተኛውን ጎል ያስቆጠረው መደበኛ የጨዋታ ክፍሌ ጊዜ ተጠናቅቆ በተጨመረው የባከነ ደቂቃ ውስጥ  ነው።

በመጀመሪያው የጨዋታ ክፍሌ ጊዜ ወልዲያ ባለሜዳዎቹ እንደፈለጉ እንዳይንቀሳቀሱ ለማድረግ ጥረት ሲያደርግ፤ ወላይታ ድቻ በመከላከል፣ ኳስ በማደራጀትና የመሃል ሜዳውን በመቆጣጠር በመጠኑ የተሻለ እንቅስቃሴ አሳይተዋል።

በሁለተኛውም የጨዋታ ክፍሌ ጊዜ ተመሳሳይ የጨዋታ እንቅስቃሴ ቢታይም ባለሜዳዎቹ የመጀመሪያውን ጎል በ67ኛ ደቂቃ ላይ በማስገባታቸው ሁለቱም ቡድኖች ወደፈጣን የጨዋታ እንቅስቃሴ ለመግባት ችለዋል።

በአጠቃላይ ጨዋታ ሁለቱም ቡድኖች ኳስን በመሀል የሜዳ ክፍል ከማንሸራሸር ባለፈ አደጋኛ የጎል ሙከራዎች ሳያደርጉና ጎል ሊሆኑ የሚችሉ ኳሶች አንዲሁ ሲባክኑም ታይቱዋል።

የወልዲያ እግር ኳስ ቡድን አሰልጣኝ ዘማሪያ ወልደጊዮርጊስ "ኳስ መስርተን ለመጫወት ነበር ዕቅዳችን ሜዳው ለጨዋታው ምቹ አለመሆን ለሽንፈታችን ምክንያት ነው" ብለዋል።

"ከዚህም በላይ ያገኘናቸውን አጋጣሚ አለመጠቀማችንም ዋጋ አስከፍሎናል፤ በሚቀጥለው ዙር ወደአሸናፊነት እንመለሳለን" ሲሉ ተደምጠዋል።

የወላይታ ድቻ ቡድን አሰልጣኝ ዘነበ ፍስሃ በበኩሉ በተላይ በመጀመሪያው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጋጣሚያቸው ይዞ የገባው የጨዋታ አካሄድ እንደፈለጉ እንዳይቀሳቀሱ እንዳደረጋቸው ተናግረዋል።

"በሁለተኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ይህን በመመልከት የተጨዋችና የጨዋታ ስልት በመቀየራችን ማሸነፍ ችለናል" በማለት ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ይህ ድል ለቀጣይ የአፍርካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ጨዋታም ከፍተኛ የሞራል ስንቅ እንደሚሆናቸው ነው የገለጹት።

ድሉን ተከትሎ የወላይታ ድቻ ቡድን ነጥቡን ወደ 19 በማድረስ ከነበረበት ከ11ኛ ደረጃ ወደ 8ኛ ደረጃ ከፍ ያለ ሲሆን ተጋጣሚው የወልዲያ ቡድን በ18 ነጥብ ከ8ኛ ደረጃ ወደ 11ኛ ደረጃ ዝቅ ብሏል።

የ2010 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ የተጠናቀቀ ሲሆን ሊጉን ደደቢት በ29 ነጥብ ቀዳሚነቱን ሲይዝ፣ ጅማ አባ ጅፋርና መቀሌ ከተማ በተመሳሳይ በ25 ነጥብ በጎል ተበላልጠው 2ኛ እና 3ኛ ደረጃን ይዘዋል።

የከፍተኛ ጎል አግቢነትን ኦኪኪ አፎላቢ ከጅማ አባ ጅፋር እንዲሁም ጌታነህ ከበደ ከደደቢት በተመሳሳይ በዘጠኝ ጎል እየመሩ የመጀመሪያው ዙር የ2010 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተጠናቋል።

Rate this item
(0 votes)

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን