አርዕስተ ዜና

የወልድያ ሼህ መሃመድ ሁሴን አሊ አላሙዲ ስታዲየም ተመረቀ Featured

14 Jan 2017
2123 times

ወልድያ ጥር 6/2009 በመሀመድ ሁሴን ዓሊ ዓላሙዲ ስም የተሰየመው የወልድያ ስቴዲየም ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በተገኙበት ዛሬ ተመረቀ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም በምርቃት ስነ-ስርዓቱ ላይ እንደተናገሩት መንግስት ለስፖርት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ቢሆንም የህዝቡና የባለሀብቱ ተሳትፎ ወሳኝ ነው።

በሼህ መሀመድ ሁሴን ዓሊ ዓላሙዲና በህዝብ ትብብር የተገነባውና ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀው የወልድያ ስቴዲየም አገር ማስጠራት የሚችሉ ወጣቶች የሚፈሩበት ነው ብለዋል።

ስታዲየሙ ውድድሮችን ከማስተናገድ በተጨማሪ ብቃት ያላቸው ስፖርተኞች መፍለቂያ እንደሚሆን የገለፁት ደግሞ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ናቸው።

ሼህ መሀመድ ሁሴን ዓሊ ዓላሙዲ በበኩላቸው "ስቴዲየሙ ለወልድያ ህዝብ ውለታ በቂ አይደለም፤ ድጋፉ ይቀጥላል" ብለዋል።

"ሁላችንም አገራችንን በጋራ እንገንባ" የሚል መልዕክት በማስተላለፍም ያስገነቡትን ስታዲየም ለወልዲያ ከተማ አስተዳደር አስረክበዋል።

በ567 ሚሊዮን 890 ሺህ ብር ወጪ የተገነባው ስታዲየሙ 25 ሺህ 155 ተመልካቾችን የመያዝ አቅም አለው

በ177 ሺህ ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ሲሆን በኢትዮጵያ ሙሉ ወንበር የተገጠመለትና ጥላ ያለው ብቸኛው ስቴዲየም ነው።

የስቴዲየሙ 95 በመቶ የግንባታ ቁሳቁስ በአገር ውስጥ የተሸፈነና ሙሉ በሙሉ በአገር ውስጥ ባለሙያዎች የተገነባ መሆኑም ተነግሯል።

ከህዝቡ የተሰበሰበው 31 ሚሊዮን ብር ለእንግዳ ማረፊያ ግንባታ ውሏል።

የኦሎምፒክ ውድድር የማስተናገድ ዓቅም ያለው የመዋኛ ገንዳ፣ የመሮጫ ትራክ፣ የቅርጫት ኳስ፣ የመረብ ኳስና የቴኒስ መጫወቻ ሜዳዎችንም አካቷል።

ስታዲየሙ አስር የመግቢያ በሮች ያሉት ሲሆን ስድስቱ የህዝብ፣ ሁለቱ የተጋጣሚ ቡድኖችና ሁለቱ ደግሞ የክብር እንግዶችና የሚዲያ ባለሙያዎች መግቢያዎች ናቸው።

በታሪካዊ ቦታዎችና ግለሰቦች ስሞች የተሰየሙት ሰባቱ በሮች መርጦ፣ ሙጋድ፣ ሳንቃ፣ ዳና፣ ዶክተር አረጋ ይርዳው፣ ፀጋዬ አራጌና ላሊበላ ይሰኛሉ።

የስቴዲየሙ ግንባታ አራት ዓመት ተኩል ጊዜ ፈጅቷል።

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ