አርዕስተ ዜና

ወላይታ ድቻ በሜዳው ጅማ አባ ቡናን አሸነፈ

10 Jan 2017
670 times

ሶዶ ጥር 2/2009 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እግር ኳስ ጨዋታ ዛሬ  ቀጥሎ ወላይታ ድቻ በሜዳው ጅማ አባ ቡናን አንድ ለዜሮ አሸነፈ፡፡

በመጀመሪያው ክፍለ ጊዜ ኳስ በማደራጀት ፣ በመከላከልና በማጥቃት ድቻ የተሻለ የነበረ ሲሆን በዚህም በ17 ቁጥሩ በዛብህ መለዮ አማካኝነት በ28 ደቂቃ ላይ ጎል ማስቆጠር ችሏል፡፡

የጅማ አባ ቡና በሁለተኛው ክፍለ ጊዜ ተሽለው በመቅረብ ኳስ  በማደራጀትና መልሶ በማጥቃት የሚያስቆጩ የግቡ አጋጣሚዎች ቢያገኝም ወደ ውጤት መቀየር አልቻለም፡፡

የወላይታ ድቻ  ሶስት ነጥብ ይዞ የወጣበትን ውጤት በማግኘቱ መደሰታቸውን የቡድኑ አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ተናግረዋል

" ከአምናዉ ተመሳሳይ ወቅት የተሻለ የማጥቃት ባህሪ መፍጠር ብንችልም የሚንፈጥራቸዉን የጎል አጋጣሚዎች ወደ ጎል ከመቀየር  አኳያ  መሰራት እንዳለብን ያሳያል " ብለዋል፡፡

"ከዕረፍት በፊት ተጋጣሚያችን የተሻለ ነበር ከዕረፍት በኋላ እኛ የተሻልን ነበር ይሁን እንጂ ያገኘናቸዉን ዕድሎች መጠቀም ያለመቻላችን ዋጋ አስከፍሎናል" ያሉት ደግሞ  የጅማ አባቡና አሰልጣኝ ደረጀ በላይ ናቸው፡፡

መልሶ በማጥቃት በፍጥነት ሃይል የተቀላቀለዉን የድቻ የጨዋታ እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር የተጠቀሙበት አስተላለፍ  አስቸጋሪ ሁኔታ እንደፈጠረባቸውም ጠቅሰዋል፡፡

"ልጆቼ ባሳዩት እንቅስቃሴ ኮርቼያለሁ የጨዋታ መደራረብም ጫና ፈጥሮብናል እየተሻሻልን እየሄድን በመሆኑ ወደ አሸናፊነት የመመለስ ዕድሉ አለን" ብለዋል፡፡

ለድቻ ጎሉን ያስቆጠረዉ 17 ቁጥሩ በዛብህ መለዮ   ሶስት ነጥብ ማግኘታቸው ቀጣይ ውጤታቸው ይበልጥ ለማሳደግ የሚያበረታታቸው መሆኑን ተናግሯል፡፡ 

የጅማ አባቡናው 12 ቁጥሩ ቢያድግልኝ ኤልያስ በበኩሉ "ተበልጠን ሳይሆን የዕድል ጉዳይ ነዉ ማሸነፍ ይገባን ነበር የፈጠርናቸዉን የጎል ዕድሎች ያለመጠቀማችን ዋጋ አስከፍሎናል" ብሏል

ስህተታቸውን በማረም በቀጣይ ጨዋታዎች ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ጠንክረው እንደሚሰሩም ተናግሯል፡፡

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ